እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው እውቅና ሉዓላዊነትን የሚጥስ ነው ስትል ኢራን አወገዘች።
የሶማሊያን የግዛት አንድነት እና ክብር ላይ የተቃጣ፣ ከዓለምአቀፍ ህግ ጋር የሚጣረስ መሆኑን ቴህራን ገልፃለች።
የምስራቅ አፍሪካን እና ቀይ ባህር ቀጠናን ለማናወጥ እና እንዳይረጋጋ ለማድረግ ያለመ ነው ያለችው ኢራን ከአፍሪካ ህብረት እና ከሙስሊም ሀገራት ህብረት ጎን በመቆም እንደምታወግዝ አስታውቃለች።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ እስራኤል ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠቷ ከመካከለኛው ምስራቅ በተጨማሪ አፍሪካን ለመበጥበጥ ፍላጎት ስላላት ነው ብለዋል።
ካናኒ አክለውም በቀይ ባህር እና አፍሪካ ቀንድ ላይ ያለውን አለመረጋጋት ይበልጥ የሚያባብስ በመሆኑ ቴህራን አትቀበለውም ሲሉ አስታውቀዋል ።
ከሰሞኑ እስራኤል እና ሶማሌላንድ የደረሱት የሀገርነት እውቅና ስምምነትን ተከትሎ የዓለም ፖለቲከኞች መነጋገሪያ ሆኗል።
የሀርጌሳ ነዋሪዎች ከእስራኤል ጋር የተደረገውን ስምምነት አስመልክቶ ደስታቸውን ሲገልፁ፣ በርካታ ሀገራት እየተቃወሙ ይገኛሉ ።
ተመድም አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ሁኔታው እንዲካረር እያደረገው እንደሚገኝ በርካታ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው።
የኒ ሳፋክ እና አናዶሉ እንዳስነበቡት
