ኢራን  የቬንዝዌላ ዕጣፈንታ እንዳይገጥማት ተሰግቷል

Date:

በኢራን በኑሮ ውድነት የተቀሰቀሰው ተቃውሟ ተባብሷል

በቅርብ ቀናት ኢራን ዉስጥ የተጀመረዉ ተቃዉሞ  መዲናዋን ቴሕራንን ጨምሮ ቢያንስ በበርካታ ከተሞች መቀጠሉ ተዘግቧል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ በኢራን ያለው አምባገነን አመራር ”ሰላማዊ ተቃውሞ” የማድረግ መብትን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

የኢራን የፍትህ አካላት በበኩላቸው፤ የተጎጂዎች ቁጥር ምንም ያህል ቢጨምርም፣ ከባድ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዓይን እማኞች እንደገለፁት፤ ፀጥታ አስከባሪዎች አ,ድመኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጢስ ተኩሰዋል።

የኢራን  የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች እንዳሉት፤ በተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች  እስካሁን 29 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ1200 በላይ ሰልፈኞች ደግሞ ታስረዋል።

ለዉጥ አራማጅ የሚባሉት የኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪን፣ በሰልፈኞቹ ላይ ተወሰደ የተባለዉን የኃይል እርምጃ እንዲጣራ አዘዋል። ይሁንና የኑሮ ዉድነትና የዋጋ ንረቱ በመንግሥት ጥረት ብቻ እንደማይፈታ አስታዉቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በቬንዙዌላ የአሜሪካ ወታደራዊ ዘመቻን ተከትሎ፣ ኒኮላስ ማዱሮ ከታሰሩ በኋላ የኢራን አመራር ተመሳሳይ ዕጣፈንታ  እንዳይገጥመዉ ተሰግቷል ተብሏል።

የኢራን መንግስት አሜሪካ በቬንዙዌላ የወሰደችውን እርምጃ በተመለከተ፣ ዋሺንግተን  ዓለም አቀፍ ህግን ጥሳለች ሲል ድርጊቱን አውግዟል፡፡

ኢራን ኒኮላስ ማዱሮ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ስትልም አሜሪካንን ጠይቃለች። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ትናንት ሰኞ እንደተናገሩት፤ “የአንድ ሀገር ፕሬዝዳንትና ባለቤታቸው ታፍነዋል፡፡ ይህ  ህገወጥ ድርጊት በመሆኑ የምንኮራበት ምንም ምክንያት የለም” ብለዋል።

DW-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...