ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም በኃይል መሰረተ-ልማት ግንባታ ላይ አዲስ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

መሪዎቹ በቁልፍ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።  በኢንቨስትመንት እና በሀብት አስተዳደር የቴክኒክ ትብብር ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።

ሁለት ግዙፍ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶችን ወደ ተግባር የሚያስገቡ የልማት ስምምነቶች የተፈረሙ ሲሆን የሁርሶ-አይሻ (400 ኪሎ ቮልት) እና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር (132 ኪሎ ቮልት) ፕሮጀክቶች ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ስምምነቶች በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር እና ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ እርምጃ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...