ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ዙርያ እየሰራች ነው

Date:

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን የብሔራዊ ጥቅሟ ወሳኝ አካል አድርጋ እየሰራች ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳም ተስፋዬ ገለጹ።

ኃላፊው ይህን የተናገሩት፤ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ የጎረቤት አገራት ለመጡ ዲፕሎማቶች እየሰጠ ባለው ሥልጠና መድረክ ላይ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳም ተስፋዬ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ “ኢትዮጵያ ብልጽግናን፣ ሰላምንና መረጋጋትን የሚመለከተውን የብሔራዊ ጥቅሟን የቀጣናው እጣ ፈንታ ወሳኝ አካል” አድርጋ ትመለከታለች።

ቀጣናው ሽብርተኝነት፣መፈናቀል፣ የርስ በርስ ግጭትና ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ የቀጣናው ተግዳሮቶች ለመቋቋም በርካታ ጠቃሚ እርምጃዎችን እየተወሰደ መሆኑን መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳም የሥልጠናው አላማ ትብብርን ማጠናከርና በሕዝቦች መካከል ጥልቅ ግንዛቤን ማጎልበት መሆኑን ጠቅሰው፤ በጋራ ችግሮች ላይ የትብብር መድረኮችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ዲፕሎማቶች በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ የጋራ ግቦችን ለማራመድ የሚያደርጉትን የትብብር ጥረቶች መደገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...