ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፉን የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በይፋ አስጀመረች

Date:

ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የአየር ትራንስፖርት መሪነቷን ይበልጥ የሚያጠናክርና በአፍሪካ ታሪክ ግዙፉ የሆነውን የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በይፋ መጀመሯን አስታወቀች።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት በአመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ላይ ከደረሰው የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ቀዳሚ የትራንስፖርት በር ለማድረግ የታለመ ነው።

ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ቢሾፍቱ፣ ለበረራ ስራ ባላት ተስማሚ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ለዚህ ፕሮጀክት መመረጧ ተገልጿል።

ግንባታው በሁለት ዋና ዋና ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ በአመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ የማስተናገድ አቅሙን ወደ 110 ሚሊዮን መንገደኞች ከፍ በማድረግ፣ አፍሪካን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ ቀዳሚ የበይነ-አህጉር ማዕከል (Intercontinental Hub) እንደሚሆን ይጠበቃል።

የዚህ ሜጋ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መገኘታቸው ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...