ወደ ዲጂታል የሚደረገውን ሽግግር ለማገዝ አስፈላጊ የሆኑ የዲጂታል መሠረተ ልማቶች እና መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡና በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ተቋማት እየተከፋፈሉ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተናግረዋል።
በእቅዱ መሠረት ወረቀት አልባ አሠራርን እውን ለማድረግ አብዛኞቹ የጤና ተቋማት ወደ ዲጂታል መድረክ ይሸጋገራሉ።
ሚኒስትር ዴታው አክለውም ስትራቴጂው የጤና ባለሙያዎችን አገልግሎት አሰጣጥ ለመከታተል የሚያስችል የዲጂታል ቁጥጥር ስርዓትን በማካተት የህክምና ደረጃን ለመጠበቅ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚረዳ አጽንኦት ሰጥተሰጥተፈዋል።
“ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲጀምር ዜጎች ከቤታቸው ሆነው የሕክምና ምክር እንዲያገኙ፣ በዲጂታል ቀጠሮ በመያዝ የወረፋ ጥበቃ ጊዜን እንዲቀንሱ እና በአንድ ማዕከል የተደራጀ የተሟላ የሕክምና መረጃ በማንኛውም የጤና ተቋም እንዲያገኙ ያስችላል።”
የዲጂታል አገልግሎቱ በቀበሌ ደረጃ ካሉ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የሕክምና ተቋማት ድረስ የሚዘልቅ ስለመሆኑ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
