ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለአልጄርስ ስምምነት ቁርጠኝነታቸውን ያድሱ

Date:

የአልጄርስ ስምምነት 25ኛ ዓመትን በማስመልከት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለስምምነቱ ያለቸውን ቁርጠኝነታቸውን እንዲያድሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ።

የኢትዮጵያና ኤርትራን የ1991-1993 ጦርነትን ያስቆመው የአልጄርስ ስምምነት ከተፈረመ 25ኛ ዓመቱን በያዘበት ወቅት፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ለቀመንበሩ ስምምነቱ “የሁለቱም እህትማማች አገራት ሕዝቦች “ለትብብርና ለጋራ ብልጽግና ያላቸውን ዘላቂ ምኞት” እንደሚወክል ተናግረዋል።

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ  አዲስ አበባንና አስመራን የስምምነቱን መንፈስ እንደገና እንዲያድሱ፣ እንዲሁም ዘላቂ የጋራ ሰላምን ለማስፈን ንግግርን እና መልካም ጉርብትናን ጥሩ መንገድ አድርገው እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

አክለውም በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ቀጠና ያለው ቀጠናዊ መረጋጋት እና የሕዝቦች ደኅንነት የተመሰረተው፣ “መተማመንና ትብብርን ለማጠናከር እና የጋራ ደህንነትን የሚያናጉ ግጭቶችን ለመከላከል በሚደረገው ዘላቂ ጥረት” ላይ ነው ብለዋል።

ሊቀመንበሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሁለቱንም አገራት እና ቀጠናውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ፣ለሰላም፣ ልማት፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብር እና በአጋርነት ላይ ለተመሠረተ ለጋራ መጻዒ ዕድል ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

አዲስ ስታንዳርድ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...