«ኢትዮጵያ ከጦርነትና ከስደት የምታርፍበት ዘመን ይሁን!»

Date:

የኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ፣ ለ፳፻፲፱ ዘመነ ሉቃስ አዲስ ዓመት ባስተላለፉት መልእክት፥ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮያውያን አዲሱን ዘመን በተስፋ እንዲቀበሉ ጥሪ አቀረቡ።

ልዑሉ በእንቁጣጣሽ በዓል ምኞታቸው ላይ እንደገለጹት፥ በዓሉ ከንግሥተ ሳባ ዘመን ጀምሮ የመጣ የኢትዮጵያውያን ልዩ ኩራትና ባህል ነው።

ስለዚህም ያለፈውን ዓመት የደስታና የሐዘን አጋጣሚዎች በማሰብ፣ ይህንን ታላቅ ባህል ያቆዩልንን አባቶችና እናቶች እንዲሁም ፈጣሪን ማመስገን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም በሀገራችን ላለፉት በርካታ ዓመታት የቆየው ጦርነት፣ መከፋፈልና ችግር ህዝባችንን ለእንባና ለስደት መዳረጉን ያወሱት ልዑል ኤርሚያስ፥ አዲሱ ዓመት ይህ መከራ የሚያበቃበት የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ዘመን እንዲሆን መጸለይ እንደሚገባ ገልጸዋል።

አሁን ባለው የዓለም አቀፍ ችግርና የኑሮ ውድነት ምክንያት ህዝባችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ በመጠቆም፥ እያንዳንዱ ሰው ከእርሱ በባሰ ሁኔታ ላይ ያሉ ወገኖቹን በቁሳቁስ፣ በሐሳብና በጸሎት እንዲረዳ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ፳፻፲፱ ዘመነ ሉቃስ ለኢትዮጵያና ለልጆቿ የሰላም፣ የጤናና የመታደስ ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...