ኢትዮጵያ የወደብና የጦር ሰፈር አማራጮችን በጥንቃቄ ልታጤን እንደሚገባ ተመላከተ

Date:

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካን የፖለቲካ ውጥረት ለመጋፈጥና ተሰሚነቷን ለማጠናከር የባህር በር ማግኘትን ብቻ ሳይሆን የጦር ሰፈር የመመስረትን ዕድሎች ጭምር ልትመለከት እንደሚገባ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተንታኞችና ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

እስራኤል ለሶማሌ-ላንድ የሀገርነት ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ  አስተያየታቸውን የሰጡት ባለሙያዎቹ፤ ኢትዮጵያ ከሀርጌሳም ሆነ ከሞቃዲሾ ጋር ያሏትን ስምምነቶች ከብሔራዊ ጥቅም አንጻር በድጋሚ እንድታጤን ጠይቀዋል።

የቀድሞ ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናው፤ እስራኤል ለሶማሌ-ላንድ የሰጠችውን የሐገርነት ዕውቅና ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከሶማሊያ ላንድ ጋር ያደረገችውን የ”ስጥና ተቀበል” የሁለትዮሽ ስምምነት በድጋሚ እንድታጤን ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌ-ላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት በሀርጌሳ በኩል የወደብ ተጠቃሚነትንና የጦር ሰፈርን እንደሚያካትት፣ በአንካራ ከሶማሊያ ጋር የተደረሰበት ስምምነት ግን የባህር በርን ብቻ ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ያስታወሱት ዲፕሎማቱ ኢትዮጵያ ለሁለቱም ፍላጎቶቿ መሟላት የፖለቲካ ብስለት የተሞላበት አካሄድ ልትከተል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የዓለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ እያሱ ኃይለ ሚካኤል በበኩላቸው፤ የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየተወሳሰበ በመምጣቱ ኢትዮጵያ ከሁለቱም ወገኖች ጋር የሚኖራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በብልሃት መምራት አለበት ብለዋል።

የትኛው ስምምነት ለሀገሪቱ የላቀ ብሔራዊ ጥቅም ያስገኛል የሚለውን ለመለየት የቀደሙ ውሎችን ወደ ኋላ ተመልሶ መገምገም እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ባለሙያው፤ በቀጣይ ሊባባስ የሚችለውን የቀጣናውን የፖለቲካ ሽኩቻ ለመቋቋም ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚና የወታደራዊ አቅሟን ማጠናከር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባት በአፅንኦት ገልጸዋል።
አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...