የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ለሁለት ቀናት በሚደረገው በዚሁ ጉባኤ “በሀሳብ እንፎካከራለን ስለ ሀገር እንተባበራለን” በሚሪ ሀሳብ የፓርቲ አመራሮች ምርጫን ጨምሮ ሌሎች ክንውኖችም ይደረጉበታል ተብሏል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር እና የኢዜማ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ኢዜማ ጠንካራ አቋም ያለው ለሀገር ቅድሚያ የሚሰጥ ድርጅት ነው ብለዋል፡፡
ኢዜማ በመላው ሀገሪቱ ተወካይ ያለው እንደ ሀገር መደገፍ የሚችል ፓርቲው ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በመጪው የምርጫ ጊዜም በሀሳብ የሚፎካከር ጠንካራ የፓለቲካ ፓርቲ ሆኖ ይሳተፋል ብለዋል ሊቀመንበሩ።
የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድ ሀገር መሰረት ናቸው በመሆኑም ፓርቲዎቹ በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።
አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲዎች ከገዢው ፓርቲ ጋር በቅርበት መነጋገር መቻላቸው የፓለቲካ ስነ-ምህዳሩን ቀይሮታል ያሉት ደግሞ አለሙ የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለስ አለሙ ናቸው።
አክለውም ብልፅግና ፓርቲ ከኢዜማ ጋር መረህ ላይ በተመሰረተ ግንኙነት ለሀገር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
