ኤል ኒኖ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር ጉዳት ሊያደርስ ይችላል

Date:

በአሁኑ ወቅት በተለይ ኃይለኛ በሆነው የኤል ኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ ከ10 እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል የአፍሪካ ልማት ባንክ ከፍተኛ የአየር ንብረት ባለሙያ አስጠነቀቁ።

ይህ አስጊ ሁኔታ በአህጉሪቱ ላይ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ፣ የምግብ እና የንጹህ ውሃ ዋስትና እጦት እንዲሁም መጠነ ሰፊ ስደት እንዲከሰት ሰፊ እድል እንዳለው ተመላክቷል።

ከዚህም ባለፈ የአየር ንብረት አደጋዎቹ መሠረተ ልማቶችን በማውደም የመንግሥት ግምጃ ቤቶችን እና የባንክ ሥርዓቶችን ለከፍተኛ ፈተና እየዳረጉ ይገኛሉ።

አገራትም የተበደሩትን ብድር ለመክፈል በመቸገራቸውና አደጋውን ለመቋቋም ከጤና፣ ከትምህርት እና ከሌሎች መሠረታዊ የልማት ዘርፎች በጀት በማዘዋወር “የአየር ንብረት የገንዘብ ወጥመድ” ውስጥ እየገቡ መሆናቸው ተገልጿል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ አክሎም፣ አህጉሪቱ ከዚህ አውዳሚ የኤል ኒኞ ተፅዕኖ ለመከላከል እና ለመቋቋም በዚህ ዓመት ብቻ እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ የበጀት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...