- ሂዝቦላህ
ሂዝቦላህ፣ እስራኤል ከደቡባዊ ሊባኖስ እስክትወጣ ድረስ ትጥቅ እንደማይፈታ ማስታወቁን አልጀዚራ እና አል አረቢያ ዘግበዋል።
የሂዝቦላህ ዋና ፀሃፊ ነኢም ቃሲም ለአል አረቢያ እንደተናገሩት የአሜሪካ እና የእስራኤል ዛቻ ፓርቲያቸውን “እጅ እንዲሰጥ” ወይም የጦር መሳሪያ እንዲፈታ አይገፋፋውም።
ዋና ፀሃፊው በቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር “ይህ ማስፈራሪያ እጅ እንድንሰጥ አያደርገንም፤ በሊባኖስ እና በአካባቢው የሚደረገውን ወረራ ህጋዊ የማድረግ አካል አንሆንም” ብለዋል።
ዋና ፀሃፊው ሂዝቦላህ ለሰላም በሩ ክፍት መሆኑን ጠቅሰው፤ ነገር ግን ኢስራኤል የአየር ወረራዋን እስክታቆም እና ከደቡብ ሊባኖስ እስክትወጣ ድረስ ትጥቅ አንፈታም ብለዋል። እስራኤልን ከመጋፈጥም ወደኋላ አንልም ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ ሁኔታ የቀጣናውን ውጥረት ሊያባብሰው ይችላል ተብሏል። ሂዝቦላህ እና እስራኤልም ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
