እንግሊዛዊው ግሪን ሞሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራውን በይፋ ጀመረ

Date:

ኩባንያው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ስራውን የጀመረ ሲሆን ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም ለማስፋፋት እቅድ እንዳለው አስታውቋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ለመጀመር የሁለት ዓመት ድርድር ማድረጉንና በሂደቱ ውስጥም የተለያዩ ተግዳሮቶች እንደገጠሙት ገልጿል።

በተለይም ዓለም አቀፍ የንግድ ልምዶችን እና የኢትዮጵያን የሕግ ማዕቀፍ ማጣጣም ትልቅ ፈተና እንደነበረበት አስታውቋል።

ግሪን ሞሽን ከኤክስፔዲያ እና ቡኪንግ.ኮም ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የቦታ ማስያዣ መድረኮች ጋር የተዋሃደ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለአገር ውስጥና ለአለም አቀፍ ተጓዦች ምቹ አገልግሎት ለመስጠት በኢትዮጵያ ከሚገኘዉ ኤክሰለንስ መኪና ኪራይ ኩባንያ ጋር በሽርክና መስራቱን ገልጿል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ስራ በመጀመሩ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝና ለአካባቢው ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

Source: capitalethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...