ከስድስት ሰዎች በላይ ህይወታቸው አልፏል፤ የቆሰሉም ከስድስትና ሰባት በላይ አሉ

Date:

ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ንጹሐን መገደላቸውን፣ የሰዎች እንቅስቃሴ መገደቡን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ በሰሞንኛው ጥቃት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ የቆሰሉትም በርካቶች ናቸው” ያሉ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል እየገለጹ ነው።

በተለይ አቦል ወረዳና ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢዎች “ንጹሐን ዜጎች እየተገደሉ” መሆኑን፣ ጥቃቱ ከዚህ ቀደምም የነበረ ሲሆን፣ በሰሞንኛው ሁነት ደግሞ “የጸጥታ አካላት ጭምር ሟችና ቆስለኛ” መሆናቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች ከስፍራው ወጥተዋል።

ግድያው የሚፈጸመው በተለይ ተሳፋሪዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ መንገድ ዳር በማድፈጥ በተሽከርካሪዎች ጭምር ሲሆን፣ የክልሉ ፓሊስ በበኩሉ፣ ተሳፋሪዎች ላይ ሞትና የመቁሰል ጥቃት መድረሱን ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወቃል።

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከቀናት በፊት፣ “በከተማችን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ከጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰው ከህዳር 30/2018 ዓ/ም ምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን” ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።

ጉዳዩን ይዞ ስለጥቃቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ የክልሉን ባለስጣናት የጠየቀ ሲሆን፣ የሰላምና ጸጥታ ቢሮው ፈቃደኛ አልሆነም። በስልክ የጠየቃቸው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ደግሞ፣ “በኋላ ደውሉ አሁን ስብሰባ እየመራሁ ነው። ከአንድ ሰዓት በኋላ ደውሉ” ቢሉም በድጋሚ ሲደወል ስልክ አያነሱም።

በተጨማሪ፣ በሰሞንኛው ጥቃት “ንጹሐን ተገድለዋል፤ የጸጥታ አካላትም ተገድለዋል፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብለዋል፤ ምን ያክል ሰዎች ተገድለዋል? ሲል   የጋምቤላ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ አስቲንን ጠይቋቸዋል።

የጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ ምን መለሱ?

“ከስድስት ሰዎች በላይ ህይወታቸው አልፏል፤ የቆሰሉም ከስድስትና ሰባት በላይ አሉ።

የተፈጠረውን ግጭት ግጭት ነው ብሎ ለማሰብ ትንሽ ያስቸግራል። ለምሳሌ ጋምቤላ ከተማ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ፤ አንድ ሰው ሁለት ሰዎች ላይ ጥይት ተኩሶ አንዱ ህይወቱ አልፎ አንዱ ቆስሏል። 

ከዚያ በኋላ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ደግሞ በጋምቤላ ወረዳ ከላሬ ሲመጣ በነበረ መኪና ጥይት ተተኩሷል፤ እነማን እንደሆኑ አልታወቁም፤ ዳርና ዳር ጫካ ስለሆነ ከጫካ ወጥተው ነው ጥቃት የፈጸሙት።

እዛም የተጎዱ ሰዎች አሉ። አንድ ቡድን ከሌላ ቡድን ጋር የመጋጨት አይነት ነገር ነው፤ ይሄ ግን ጥቃት ነው። የተወሰኑ ግለሰቦች በሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙበት ነው።

ግጭት የሚመስለው ሰው ተደናግጦ አንዱ ወደራሱ አካባቢ ሌላውም ወደራሱ አካባቢ ይሸሻል። ይህ ነው ግጭት ተብሎ የተወሰደው እንጅ በግለሰብ ደረጃ የተፈጸሙ ጥቃቶች ናቸው ያሉት።

ጋምቤላ ወረዳ በተፈጸመው የመኪና ጥቃት የተጎዱት ሦስት ሰዎች ናቸው። ወረዳው ላይ የተወሰኑት ነዋሪዎች “ሆ” ተብለው ተነስተው ወደ አመራሮች ወዳሉበት ግቢ ሊገቡ ሲሉ ፓሊስ ባደረገው መከላከል፤ አንድ የፌደራል ፓሊስ ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ሌላ ፓሊስም ቆስሏል። ከማህበረሰቡም አንድ ሰው ህይወቱ አልፏል። አሁን ተረጋግቷል” ብለዋል።

በሰሞንኛው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ” ከ10 በላይ” እንደሚሆን፣ ከዚህ በፊት የተገደሉት ደግሞ “ከ40 እንደሚበልጡ ” ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፤ እርስዎ ደግሞ የሰሞኑ ሟቾች ” ከ6 በላይ” ናቸው ብለዋል፤ በትክክል የሟቾች ቁጥር ስንት ነው? ሲል አቅርቧል።

እሳቸውም፣ ” የሟቾቹን ቁጥር በትክክል መረጃ መውሰድ አለብኝ፣ አሁን ካልኩት በላይ ሊሆን ይችላል የሰማሁትና የተነገረኝን ነው የገለጽኩት። ምክንያቱም የቆሰሉም አሉ፤ ቆስለው የሞቱ አሉ፣ ስለዚህ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል። ከ10 በላይ ሊሆኑ ይችላሉ ” ብለዋል።

” ‘ከ40 በላይ ሰዎች ሞተዋል’ የሚባለው፣ ሰዎች ተጣልተው አንዱ አንዱን ሊገድል ይችላል። ይሄ የቆየው የብሄር አስተሳሰብ ወደ ቡድን ይወሰዳል። ነገሩን በጣም ለማጋጋል የሞቱ ሰዎችን ቆጠራ ይጀምራሉ፣ ይሄን የሚያደርጉት ቅስቀሳ ለማድረግ ነው። ችግሩ እንዲቀጥል፣ እንዳይረጋጋ አረቄ ቤት የሞተውን ሁሉ ይቆጥራሉ ” ሲሉም አክለዋል።

ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲያስረዱም፣ ” የማረጋጋት ሥራ እየሰራን ነው ያለነው። ወንጀል የፈጸመ በግሉ እንዲጠየቅ፣ የህዝብ ውይይት እያደረግን ነው። ሥራዎች በነበሩበት መንገድ እንዲቀጥሉ፣ ተቋማት ወደነበሩበት ሥራ እንዲገቡና አካባቢው በሙሉ የተረጋጋ እንዲሆን እየሰራን ነው ” ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በበኩሉ፦

የክልሉ መንግስት፣ በጋምቤላ ከተማ አመራሮችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ነበር።

ስለሰሞንኛው ጥቃት ማብራሪያ የጠየቃቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስብሰባ መቀጠመጣቸውን ከጠዋት ጀምረው ሲገልጹ ቆይተዋል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ” ሰሞኑን በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ” የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በመድረኩ መናገራቸውን ይፋ አድርጓል።

” ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር የማዋል ስራ ” እንደሚቀጥል መናገራቸውን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...