ከኢራን ጋር ውጥረትን ለመቀነስ የሚያስችል ውይይት አድርገናል- ኳታር

Date:

የኳታሩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ውጥረትን መቀነስ የሚያስቸል ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።

የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዛሬ በቴህራን የደረሰው የኳታር ልዑካን ቡድን ከአባስ አራጋቺ ጋር “ውጥረትን በሚቀንስ እና ለንግግር ምቹ ሁኔታን በሚፈጥሩ” ጉዳዮች ዙሪያ መወያየቱን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ላይ ኢራን እና ኳታር ከሆርሙዝ ወሽመጥ ፈንጂዎችን ለማጽዳት የሚያስችል “የጋራ ፕሮጀክት” ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረስ ስምምነት፣ እንዲሁም “ውጥረትን ለመቀነስ እና ለውይይት ተስማሚ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ስለሚደረጉ ጥረቶች” ተወያይተዋል ብሏል።

የኢራን የዜና ወኪል ታስኒም በበኩሉ የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ እና ዋና ተደራዳሪ መሐመድ ባጌር ጋሊባፍ በቴህራን ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በቀጣናው ያለውን ውጥረት የማርገብ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ዘግቧል።

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት “በቀጣናው የታዩ አዳዲስ ክስተቶችን፣ እንዲሁም ውጥረትን ለመቀነስ እና የክልሉን ደህንነትና መረጋጋት ለማጠናከር በሚረዱ ውይይቶች ላይ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የተደረጉ ጥረቶችን” እንደገመገመ ተገልጿል።

የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ፣ ወደ ቴህራን በመጓዝ፣ ከኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ እና ዋና ተደራዳሪ ሞሃመድ ባጌር ጋሊባፍ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ጋር ተገናኝተዋል።

ከፍተኛ የኳታር ልዑካን ቡድን ወደ ቴህራን ያመራው የፓኪስታን የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል አሲም ሙኒር በኢራን ከተገኙ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...