ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት መሻከር ምክንያት በጦርነቱ ወቅት የተፈጸመ “ዘረፋና ወንጀል” መሆኑ ተገለጹ

Date:

ኢትዮጵያ ከኤርትራ መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻክር ያደረገው ዋናው ምክንያት የቀይ ባሕር ጥያቄ ሳይሆን በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ጦር የፈጸመው ዘረፋና ውድመት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በተካሄደው የ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በንግግራቸውም በሁለቱ አገራት መካከል ችግር የተፈጠረው የኢትዮጵያ መንግሥት የቀይ ባሕር ጥያቄ በማንሳቱ ነው ተብሎ የሚታሰበውና የሚተነተነው ሐሳብ ስሕተት መሆኑን አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንኙነቱ እንዲሻክር ያደረጉትን ነጥቦች ሲዘረዝሩ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የመጀመሪያ ዙር ውጊያ ወቅት የኤርትራ ጦር “ከጀርባ በመግባት” በፈጸማቸው ተግባራት ጸብ መጀመሩን ገልጸዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ የኤርትራ ጦር በአክሱም ወጣቶችን በጅምላ መግደሉ፣ ቤቶችን ማፍረሱ እንዲሁም በዓድዋ ከተማ አካባቢ ፋብሪካዎችን መዝረፉና ማውደሙ ለግንኙነቱ መበላሸት መነሻ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በማብራሪያቸው ‹‹በወቅቱ ይህንን ድርጊት በወቅቱ ለመቆጣጠር የሚያስችል ሁኔታ እንዳልነበረም›› ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

መንግሥት ከኤርትራ ጋር የነበረውን አለመግባባት ለመፍታትና ሰላም እንዲሰፍን ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙት እነዚህ ወንጀሎችና የንብረት ውድመቶች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ከፋ ደረጃ እንዳሸጋገሩት ጠቁመዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...