ከፌስታል ወደ ውዳቂ ወረቀት ይሄ ነገር ከፍታ ነው ዝቅታ ግራ የሚገባ ነው -ሙሼ ሰሙ

Date:

ማንኛውም የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም ከተከለከል አንድ ቀን ሆኖታል። ጋዜጣ፣ መጽሐፍትና መጽሔት እንዲሁም ቀለም የታተመባቸው ወረቀቶችና የማደበርያ (Polypropylene) ምርቶች በስፋት ለመጠቅለያነት ገበያ ላይ እንደሚውሉ ገምቼ ነበር። ሁሌም ስራን ጥርትና ጥንቅቅ አድርጎ በጥናት ላይ ተመስርቶ መስራት አለመቻልና አለመፈለግ ውጣ ውረዱ ብዙ ነው።

ዛሬ ጠዋት ዳቦ ስገዛ ዳቦው የተጠቀለለበት ወረቀት የአንድ ባንክ (ፎቶ ይመልከቱ) የገንዘብ ወጪ ማዘዣ ነው። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ መፍትሔ በግድ ፈገግ አሰኝቶኛል። ከፌስታል ወደ ውዳቂ ወረቀት ይሄ ነገር ከፍታ ነው ዝቅታ ግራ የሚገባ ነው።

ከፌስታል ኬሚካል ወደ ሕትመት ቀለም ኬሚካል ተሸጋግረናል ማለት ነው ?! ከአካባቢ ብክለት ባሻገር የኬሚካል ይዘታቸው ለካንሰር በማጋለጥ የትኛው እንደሚብስ ለጤና ባለሙያዎች ትቼዋለሁ።

በደርግ ዘመን በቂ የወረቀት አቅርቦት ስላልነበር። ስጋን ጨምሮ ሸቀጥ የሚጠቀለልው በጋዜጣ ነበር። የሕትመቱ ቀለም ለካንሰር ያጋልጣል በሚል የጋዜጣ መጠቅለያ መከልከሉን አስታውሳለሁ።

ሌላው ያስደመመኝ ነገር የተከለከለው የፕላስቲክ ከረጢት ምን ዓይነት እንደሆነ አለመታወቁ ነው። በየገበያውና በየሱፐር ማርኬቱ የሚሸጡ አብዛኛዎቹ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ምርቶች ዘይትን ጨምሮ ከፕላስቲከሰ ከረጢት በማይሻልና በሚቀራረቡ የፕላስቲክ ምርቶች የማይታሸግ ነገር የለም። ከሆነስ ዘንዳ አማራጩ ምንድን ነው ?! የፕላስቲክ ከረጢትን የሚተካ በቂ የወረቀትና አማራጭ አቅርቦትስ አለ?

የተከለከለው በጅምላ የፕላስቲክ ማሸጊያና መያዢያዎች ከሆኑ ዘይትን ጨምሮ ከውጭ የሚመጡና ሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ማሸጊያቸው ወደ ወረቀት ይለወጥ ይሆን? ወይስ ከፕላስቲክ ማሸጊያዎች ውስጥ የተከለከለው ዓይነት ይታወቃል ?! ጥያቄ የሚያጭር ጉዳይ ነው ?! ደንብ አስከባሪው አካልስ ማነው ፖሊስ፣ የወረዳ ደንብ? ሚሊሺያ? … እንካ ሰላምታና ውዝግብ እንደሚፈጥር ጥርጥር የለኝም። ለማንኛውም ስራን ጥርትና ጥንቅቅ አድርጎ በጥናት ላይ ተመስርቶ መስራት አለመቻልና አለመፈለግ ውጣ ውረዱ ብዙ ነው።

በነገራችን ላይ በተለምዶ ማዳበርያ የሚባለው ማሸጊያ (Polypropylene) ከረጢት የሚመረተው ከፕላስቲክ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...