ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉቦ የተቀበሉ የገቢዎች ሠራተኞች

Date:



የግብር ተመን ቀንሰን እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተጠርጣሪ ሰራተኞችና ገንዘቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ሲያሰባስቡ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሲዳሞ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ አሮጌ ዕቃ እየገዙ ከሚሸጡ ነጋዴዎች፤ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞች ነጋዴዎቹን በማነጋገር ለመንግስት የምትከፍሉትን የግብር የዋጋ ተመን ቀንሰን እንሰራላችኋለን ይሏቸዋል።

ይህንንም ለማስፈጸም እናንተ በአምስት ሰዎች አስተባባሪነት ከእያንዳንዱ ነጋዴ ብር አሰባስባችሁ የድርሻችንን ስጡን በማለት ከ89 ነጋዴዎች ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስበዋል።

የዚህን ድርጊት መፈጸም ከህብረተሰቡ መረጃ የደረሰው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሁለቱን የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞችና አምስቱን ነጋዴዎች መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ህጋዊነት የጎደለውን አካሄድ በመከተል ከመንግስት አሰራር ውጪ የንግዱን ማህበረሰብ በማሳሳት ባልተፈለገ አግባብ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙና የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሀገርን እና ህዝብን ለጉዳት የሚዳርጉ መሰል አካላት ሲገጥሙ የንግዱ ማህበረሰብም የጀመረውን ወንጀለኛን የማጋለጥ አበረታች ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል ህጋዊ አሰራርን ሊከተል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...