ከ100 በላይ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች እስራኤልን አወገዙ

Date:

ድርጅቶቹ መንግስታት አፉጣኝ እርምጃ እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል። ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ኦክስፉምና፣ ሜዲስንስ ሳን ፍሮንታየር የእስራኤል ድርጊት ካወገዙ አለምአቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች መካከል ይገኙበታል።

እስራኤል በጋዛ ያሉ የሰብዓዊ እርዳታዎች እንዳይገቡ በማገድ፣ በመቆጣጠርና ፣ በእርዳታ የሚከፉፈልባቸው ስፍራዎች ጥቃት በመፈፀም በርካታ ፍልስጤማውያን ለከፉ ረሀብና ሞት እንዲዳረጉ ሆነዋል።

ህፃናት በምግብ እጥረት ለመቀንጨር ሲዳረጉ፣ በእድሜ ከፍ ያሉት ደግሞ በረሀብ በየመንገዱ ሞተው መገኘት እየተለመደ መጥቷል።

እንደ ጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ መሰረት ባለፉት 24 ሰአት እንኳ ከ10 በላይ ፍልስጤማውያን በረሀብ ሞተዋል።

እስራኤል ካለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት አንስቶ ምንም አይነት የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በመከልከል በርካታ ጥፋቶች እየደረሱ ይገኛሉ ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ አሁን ደግሞ 109 አለምአቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ድርጊቱን ከማውገዝ ባሻገር ጫና ለመፍጠር እየሰሩ ነው ሲል ቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘግበውታል።

በ-የአብስራ ሚሊዮን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...