“ክራፍት አዲስ 2018” (CRAFT ADDIS) ሊካሄድ ነው

Date:

​ የአፍሪካን የፈጠራ ኢኮኖሚ (Creative Economy) እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል የተባለለት ታላቁ የ”ክራፍት አዲስ” (CRAFT* ADDIS) ፓን-አፍሪካ ፌስቲቫል ከሚያዝያ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

​በዘለማን (Zeleman) ኮሙኒኬሽን አዘጋጅነት ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ፍሎውለስ ኢቨንትስ (Flawless Events) ጋር በመተባበር የሚሰናዳው ይህ መድረክ፥ ከ10 ሺህ በላይ የዘርፉ ባለሙያዎችንና ተሳታፊዎችን በአንድ ላይ ያገናኛል ተብሎ ይጠበቃል።

​የመድረኩ ዋና ዋና ትኩረቶች፦

📌​የገበያና የፋይናንስ ትስስር፦ የፈጠራ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን በቀጥታ ለገዢዎችና ለባለሀብቶች የሚያቀርቡበት “The Deal Room” የተሰኘ የንግድ መድረክ ተዘጋጅቷል።

📌​የቴክኖሎጂ ተጽዕኖ (AI & Digital): አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ዲጂታል ጥበብ እና የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች በኢኮኖሚው ላይ ያላቸውን ሚና የሚዳስሱ የባለሙያዎች ውይይትና ማስተር ክላሶች ይካሄዳሉ።

📌​የልህቀት ሽልማት (CRAFT Excellence Award): በዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱና አዳዲስ ፈጠራዎችን ላቀረቡ ባለሙያዎች ልዩ እውቅናና ሽልማት ይሰጣል።

📌​ኪነ-ጥበብና ሙዚቃ፦ የኢትዮ-ጃዝ አባት ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ ከለንደን ከመጣው ‘Steps Ahead’ ባንድ ጋር በመሆን የሚያቀርቡት ልዩ የ”Legacy Concert” የፌስቲቫሉ አንዱ ድምቀት ይሆናል።

📌​የወጣቶች ተሳትፎ፦ የፊልም (SmartPhilm)፣ የቪዲዮ ጌም ውድድሮች እና የዲጂታል ፍሪላንስ መድረኮች ላይ ወጣቶችና ሴቶች በስፋት እንዲሳተፉ ዕድል ይፈጥራል።

​የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቢኒያም ታየ እንደገለጹት፤ እንዲህ ያሉ አህጉራዊ መድረኮች አዲስ አበባን የአፍሪካ የፈጠራ ማዕከል ለማድረግና የከተማዋን የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመገንባት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።

​በፌስቲቫሉ ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተሳታፊዎች በ www.craftaddis.com/pre-register በኩል ቀድመው መመዝገብ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...