ወደ ውጭ አገር ስለሚላኩ ዕቃዎች የቀረጥና ታክስ ክፍያ

Date:



የምርት ወይም የጥገና ሂደታቸውን አጠናቀው እንዲመለሱ ወደ ውጭ አገር ስለሚላኩ ዕቃዎች (በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 66 መሰረት)


1) ዕቃዎች የምርት ሂደታቸውን በውጭ አገር እንዲያጠናቅቁ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ኮሚሽኑ ሲፈቅድ በጊዜያዊነት ወደ ውጭ አገር ሊላኩ ይችላሉ፤


2) ዕቃዎች በአገር ውስጥ ለመጠገን የማይችሉ መሆናቸው ተረጋግጦ ኮሚሽኑ ሲፈቅድ በውጭ አገር ተጠግነው እንዲመለሱ በጊዜያዊነት ወደ ውጭ አገር ሊላኩ ይችላሉ፤


3) በጊዜያዊነት ወደ ውጭ የተላኩ ዕቃዎች የምርት ወይም የጥገና ሂደት ውጤት የሆኑ የማካካሻ ምርቶች ዕቃዎቹ በጊዜያዊነት ከተላኩ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ተመልሰው መግባት አለባቸው፤ ሆኖ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ኮሚሽኑ የጊዜ ገደቡ እንዲራዘም ሊፈቅድ ይችላል፤


4) የምርት ወይም የጥገና ሂደታቸውን አጠናቀው እንዲመለሱ ዕቃዎች በጊዜያዊነት ወደ ውጭ አገር የተላኩበትን ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ወደ ውጭ መላክ የዕቃ ዲክላራሲዮን በማቅረብ እንዲቋረጥ ማድረግ ይቻላል፤
የቀረጥና ታክስ ክፍያ (በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 67 እና በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት)


1) የምርት ወይም የጥገና ሂደታቸውን አጠናቀው እንዲመለሱ በጊዜያዊነት ወደ ውጪ የሚላኩ እቃዎች ቀረጥና ታክስ አይከፈልባቸውም፡፡ ሆኖም የማካካሻ ምርቶቹ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 66

(3) መሠረት ተመልሰው ወደ አገር ውስጥ ካልገቡ በእቃዎቹ ላይ የሚፈለገው ቀረጥና ታክስ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት አስተዳደራዊ ቅጣት ይከፈልበታል፤


2) በሌሎች ህጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የማካካሻ ምርቶቹ ወደ ውጭ አገር ሲላኩ ወይም ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ በዕቃዎቹ ላይ የሚፈለግባቸው ቀረጥና ታክስ ይከፈልባቸዋል፤


3) የጥገና ውጤት የሆኑ ማካካሻ ምርቶችን የሚመለከት ቀረጥና ታክስ የሚሰላው በጥገና ወጪው ላይ ተመስርቶ ይሆናል፤


4) የምርት ወይም የጥገና ሂደታቸውን አጠናቀው እንዲመለሱ በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገቡ ወይም ወደ ውጭ አገር የተላኩ ዕቃዎች ለውጥ ሳይደረግባቸው በነበሩበት ሁኔታ የሚመለሱ ወይም ያለክፍያ ተጠግነው የሚመለሱ ከሆነ ቀረጥና ታክስ አይከፈልባቸውም፡፡
……….
የደንበኞች ትምህርት ቡድን
መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ምንጭ
የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 እና የተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 1160/2011

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...