ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ ህገ-ወጥ ወርቅ አውጭዎችን ከቃፍታ ብሄራዊ ፓርክ ማስወጣት ተቻለ

Date:



በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የኤርትራ ድንበር ላይ የወርቅ ማዕድን እንዲሁም የዕጣን ዛፎች በብዛት ከሚገኙበት ቃፍታ ብሄራዊ ፓርክ ወደ 12 ሺህ ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን  አውጭዎችን ማስወጣቱን የኢትጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

እና እጣን አምራቾች ደኖችን እያወደሙ ፈተና እንደሆነበት የኢትጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ገልጽዋል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ 12 ሺህ የሚሆኑ ህገ-ወጥ ወርቅ አውጭዎችን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በሌሎችም የፀጥታ ሀይሎች እገዛ ከፓርኩ እንዲወጡ መደረጉን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም ከዚህ በፊት ወደ 12 ሺ የሚሆኑ ህገ ወጥ እጣን አምራቾችን ከፓርኩ እንዲወጡ መደረጉን  ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ በአካባቢው የምንቀሳቀሱ ህገ ወጥ ወርቅ አውጭዎችም ለፓርኩ ፈተና ሆነውበታል ብለዋል፡፡

በፓርኮች ውስጥ ማዕድን ማውጣት እና የእርሻ ስራ ማከናወን በአዋጅ የተከለከለ ቢሆንም ህገ-ወጥ የወርቅ አውጭዎች እና የእጣን አምራቾች ግን ወደ ቃፍታ ብሄራዊ ፓርክ በተደጋጋሚ እየገቡ እንደሚያዙ ነው የገለፁት፡፡ ይህንን ተከትሎም  እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ፓርኩ ተጎድቶ እንደነበር እና ከ2015 እስከ 2017 በተሰራው ስራ ወደ ኤርትራ የተሰደዱ ዝሆኖች ወደ ፓርኩ መመለሳቸውን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...