ዘመን ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 100 ቢሊዮን ብር አለፈ

Date:

ዘመን ባንክ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት እጅግ ስኬታማ አፈጻጸም አስመዝግቢያለሁ ብሏል፡፡

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ እንዳሉት “በግማሽ ዓመት ብቻ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዝግቧል”

ባንኩ በላከልን መግለጫ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን 106 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን።የተከፈለ ካፒታልን ወደ 14 ቢሊዮን ብር አሳድጓል የባብኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 80 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

በተጨማሪም አቶ ደረጀ ፣ የባንኩ ዕድገት ከደንበኞች ዕድገትና ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር የተቆራኘ ነው ብለዋል።

ባንኩ በተለይ በብድር አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝትና በኢንቨስትመንት ረገድ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ውጤቱ ባንኩ ያለውን የተረጋጋ ዕድገት እና ጠንካራ የደንበኞች አመኔታ ያሳያል ያሉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ ፤ አፈጻጸሙም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር “የላቀ እና ስኬታማ” እንደሆነ ተገልጿል።

በ2001 ዓ.ም የተመሰረተው ዘመን ባንክ፣ ልዩ የፋይናንስ አገልግሎትን ለደንበኞቹ በማቅረብ ይታወቃል።

ባለፉት 17 ዓመታት የአገልግሎት አድማሱን በማስፋትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ መሆን ችሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...