ዛሬ የሀገርና የትውልድ ገንቢ ለሆኑት መምህራኖቻችን የምስራች ቀን ነው

Date:

“በ57 ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው ማህበራት ተደራጅተው፣ የሚጠበቅባቸውን 25 በመቶ ቅድመ ቁጠባ ወደ 4 ቢሊዮን ብር ገደማ ለቆጠቡ 6,194 መምህራን፣ ከሊዝ ነፃ የለማ መሬት በማቅረብና የፋይናንስ አማራጮችን በማመቻቸት የመኖሪያ ቤት ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረናል።

በዚህም መምህራኑ 25 በመቶ በመቆጠባቸውና ቀሪው 75 በመቶ ከባንኮች ጋር የፋይናንስ አማራጭ እንዲመቻች በማድረግ፣ ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ዋጋው 24 ቢሊዮን ብር የሚገመት 40 ሄክታር መሬት በነፃ ቀርቧል።

በተጨማሪም መንግስት ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የካሳ ወጪ በመሸፈን፣ መምህራንን በማህበር በማደራጀት፣ የዲዛይን ስራዎችን በማከናወንና ኮንትራክተሮችን በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጓል። በዚህም ለመምህራን ያለንን ክብር በተግባር አሳይተናል። መምህራንም ድርሻቸውን ተወጥተው ዛሬ የሳይት ዕጣ አውጥተው ተረክበዋል።

ዛሬ ያስጀመርነው የመምህራን ማህበር ቤት ግንባታ ያለ ምንም መስተጓጎል በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ከመምህራን በተጨማሪ የተደራጁ ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችንም በርቱ ለማለት እወዳለሁ።

በመጨረሻም “አይቻልም፣ አይሳካም” ለሚሉ አስተሳሰቦች ቦታ ሳትሰጡ፣ በፍጥነት ተደራጅታችሁ በመቆጥብ ፋና ወጊ ለሆናችሁት መምህራን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፤ ለቤቶቹ ምረቃ እንደምንገናኝ ሙሉ እምነት አለኝ።”

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...