ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ደማቅ የድሮን ትርዒት ላይ ነወ ።
“…እኛ ያለ ኢትዮጵያ እናት የለንም፥ ኢትዮጵያም ያለ እኛ ልጆች የሏትም ..” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ፥ ኢትዮጵያ በተቸገረችበትና በደኸየችበት ጊዜ ወደ እንጀራ እናት የሄዱ ወገኖች የእንጀራ እናት ስለማታዛልቅ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል፡፡
” እናት ሀገራችን ልጆቿን ስለማትተው የኢትዮጵያ ልጆች መተኪያ የሌላት ሀገር መሆኗን ተገንዝበን በመደመር እንደ ትናንት ጀግኖቻችን የኢትዮጵያን ጽናትና ልዕልና ማረጋገጥ ከሁላችን ይጠበቃል” ብለዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን እና ቼክ ሪፐብሊክን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አየር ኃይሎችም በትርዒቱ ላይ ተሳትፈዋል ።
የአየር ኃይል 90ኛ ዓመት በዓል ትናንት አርብ በድሮን ትርዒት እና በወደፊቱ የአፍሪካ የአየር ኃይል መጻዒ እጣ ፋንታ ላይ በመከረ ፎረም በይፋ መከፈቱ ይታወሳል።
በመርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ታድመዋል።
