
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመተባባር የሂሳብና እንግሊዘኛ ማጠናከሪያ ትምህርቶችን በአማረኛ፣ በአፋን ኦሮሞና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች ከዛሬ የካቲት 25 ጀምሮ በቴሌቭዥን ስርጭት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
የቢሮው ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፤ ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ከተያዙ ስትረቴጂ ግብ ውስጥ አንዱ ትምህርት በቴሌቪዥን የማሰራጨት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም የትምህርት ሥርጭቱ ከ4 እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በመግለጽ ሥርጭቱ 13 ዘርፎች ላይ ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
ትምህርቱ ከየካቲት 25 ጀምሮ በኤኤምኤን ፕላስ ከሰኞ እስከ አርብ ከ11 እስከ 2 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ጠዋት 2 እስከ 6 ሰዓት በሶስቱ ቋንቋዎች እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በበኩላቸ ስርጭቱ ኤኤምኔን ፕላስ ቻናልን ጨምሮ በትምህርት ቢሮና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እንደሚተላለፍ ጠቁመዋል።