የልጆች ወላጆችን አለመታዘዝ ሰበበ ምክንያት

Date:

ለብዙ ወላጆችና አሳዳጊዎች በልጆቻቸው አለመሰማትና ትዕዛዛቸውን አለመፈጸም የተለመደና ትልቁ የዕለት ተዕለት ተግዳሮት ነው። ታዲያ ልጆች ለምን አይሰሙንም? ለምን አይታዘዙንም? ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምክንያቶች ማጤን ያስፈልጋል።

1. ረጅምና አሰልቺ ገለጻ ስለምናደርግ፡-

ልጆች ወላጆቻቸው እንደማያዳምጧቸው እና  የራሳቸዉን ሃሳብ ብቻ እንደሚያንጸባርቁ ካሰቡ ፈጽሞ ወላጆቻቸውን ለማዳመጥ አይፈልጉም።

2. ልጆች የማይወዱትን ቃላት ስለሚጠቀሙ፡-

አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች አሉታዊ በሆኑ ቃላቶች  “አይሆንም፣ አታድርግ፣ አትችልም” በሚሉ ቃላት መናገር ከጀመሩ ልጆች እነዚህ ቃላት የወቀሳና  የክስ ስለሚሆንባቸው ወላጆቻቸውን ከጅምሩ እንዳይሰሙ ያደርጋቸዋል።

3. በትዕዛዝና በጩኸት ስለሚያናግሯቸው፡-

ብዙውን ጊዜ ወላጆች በጩኸትና በአለቅነት  መንፈስ የሚያናግሯቸው ከሆነ ልጆች የወላጆቻቸው ንግግር በጩኸት ካልሆነ በስተቀር ያለመስማትና ያለመታዘዝን ልምድ ያደርጉታል።

4. የልጆችን ትኩረት ሳያገኙ ስለሚያናግሯቸው፡-

ወላጆች ልጆቻቸውን በሚያናግሩበት ወቅት ልጆች በሌላ ጉዳይ ላይ ሆነዉ፤ እየተጫወቱ ወይም ቴሌቪዥን እያዩ ከሆነ ትኩረታቸውን ማግኘት ስለሚከብድ በዚህ ወቅት ልጆችን ከማናገር ይልቅ ትኩረታቸውን ስቦ ማውራት ይመከራል።

5. ወላጆች ልጆቻቸው አይሰሙንም ብለው በሚያስቡ ጊዜ ስለምሚጮሁ፡-

በሚጮሁበት (በሚቆጡበት) እና በሚናደዱበት ጊዜ ልጆች ይሰሙናል ብለው የሚያስቡ ወላጆች ጥቂት አይደሉም። ከመናደድና ከመቆጣት ይልቅ ሰከን ብለው በፍቅርና በተረጋጋ መንፈስ ቢያናግሯቸው የተሻለ ሊሰሙንና ሊያዳምጡ ይችላሉ።

6. ምሳሌ ስላልሆኗቸው፡-

ልጆች ሁሌም ወላጆቻቸውን ይመስላሉ። ወላጆች ጥሩ አድማጭ ካልሆኑ ልጆችም ሊያደምጡ አይችሉም። 

7. ላለመስማት ከመረጡ፡-

ከላይ በዘረዘርናቸው ምክኒያቶች ሳይሆን  የወላጅን ትኩረት ፈልገው፣ ባለማክበር ወይም ሌላ ያልተፈታ ችግር በመከል ካለ ልጆች ላይሰሙ ይችላሉ።

8. በጤና መጓደል ምክንያት አዳንድ ልጆቻችን በጤና ችግር ምክንያት የመስማት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል። ይህን መከታተልና በተለይ በህጻንነት ወቅት የሀኪም እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ያሻል።

የድባቴ ሕመም

ሰው ኾኖ የሐዘን ስሜት የማያጋጥመው የለም፡፡ የሐዘን ስሜቱ ግን ጊዜያዊና ዕድሜው ከቀናት ያልበለጠ ነው፡፡ ኾኖም አንድ ሰው ከገባበት ሐዘን በቶሎ መላቀቅ ካልተቻለ የድባቴ ሕመም አጋጥሞታል ማለት ይቻላል፡፡ የድባቴ ሕመም ውስጥ ያለ ሰው ደግሞ ከራሱ አልፎ በዙርያው ያሉትን ሰዎች ዕለታዊ የሕይወት እንቅስቃሴ ያውካል፡፡ የድባቴ ህመም በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት፣ ችላ ከተባለ ግን የአዕምሮ ጤናን የሚያውክ አደገኛ በሽታ ነው፡፡

የድባቴ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የድባቴ ምልክቶች በሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ የሕመሙ ደረጃ ቆይታና አስከፊነት እንደየግለሰቡ የድባቴ ሁኔታ ይለያያል፡፡ ሆኖም ቀጥሎ ከተዘረዘሩት በርከት ያለው ካጋጠመ ድባቴ መኖሩን ይጠቁማል፡፡

• ተከታታይ የኾነ የሐዘን፣ የንዴት፣ የብስጭት፣ የቁጣና የባዶነት ስሜት

• የተስፋ ማጣትና ጨለምተኝነት አመለካከት

• ራስን መውቀስ፣ ዋጋቢስና ረዳት የለሽ የመኾን ስሜት

• በትንሽ በትልቁ መበሳጨትና ቅብጥብጥነት

• ለወትሮው በፍቅር ለምናከናውናቸው እንደ ስራ፣ ጨዋታ፣ መዝናናት እና ወሲብ ለመሳሰሉት ፍላጎት ማጣት

• ድካምና ተነሳሽነት ማጣት

• አትኩሮት ማጣት፣ ዝንጉነትና ውሳኔ ለመስጠት መቸገር

• መጫጫን፣ የእንቅልፍ መዛባት(እንቅልፍ ማጣት ወይም ለረዥም ጊዜ መተኛት)

• ከመጠን ያለፍ መመገብ ወይም የምግብ ፍላጎት መቀነስ

• ራስን ማጥፋት መፈለግና መሞከር

• በሕክምና መታገስ ያልቻለ ራስ ምታት፣ ቁርጠት፣ ቁርጥማትና የምግብ አለመፈጨት ችግር፡፡

1 ከባድ የድባቴ ሕመም

ማንኛውም ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ አይነት የድባቴ ምልክት ሊታይበት ይችላል፡፡ ኾኖም አንድ ሰው ላይ የተለያዩ የድባቴ ምልክቶች አዘውትሮ ማጥናት፣ ሥራ መሥራት፣ መተኛት፣ መዝናናት የመሳሰሉት ዕለታዊ እንቅስቃሴዎቹን የሚያውክበት ከኾነ ከባድ የመደበት ስሜት ውስጥ ነው ማለት ይቻላል፡፡

2. የተራዘመ የድባቴ ሕመም

የተራዘመ የድባቴ ስሜት ለሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ለኾነ ግዜ የሚቆይ የመደበት ምልክቶች ይታይበታል፡፡ የተራዘመ ድባቴ ዕለታዊ ተግባርን ሙሉ በሙሉ አያውክም፡፡ ኾኖም ሰዎች መልካም መንፈስ እንዳይኖራቸውና መደበኛ ተግባራቸውን በሚጠበቀው ደረጃ እንዳይፈፅሙ ያደርጋል፡፡

3. አነስተኛ የድባቴ ሕመም

አነስተኛ የድባቴ ስሜት ምልክቶች ለሁለት ሳምንታት ወይም ከዚያ በላይ ይቆያሉ፡፡ አነስተኛ የመደበት ስሜት ከጅምሩ ሕክምና ካልተደረገበት ስሜቱ ቀስ በቀስ ወደ ከፍተኛ ድባቴ ሊቀየር ይችላል፡፡

ሳይኮቲክ ድባቴ

ሳይኮቲክ ድባቴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰ የድባቴ ሕመም የሚመጣ የአዕምሮ መቃወስ ነው፡፡ ሳይኮቲክ ድባቴ ያለበት ግለሰብ በተሳሳተ ግምት ይረበሻል፡፡ ከእውነታ ጋር የሚጋጭ አስተሳሰብ ያራምዳል፡፡ በተጨማሪም ለጤናማ ሰው በማይሰማ እና በማይታይ ሃሳብ የመንፈስ ጭንቀት ይደርስበታል፡፡

ድሕረ ወሊድ ድባቴ

ይህ የድባቴ አይነት ከወሊድ በኋላ በሚከሰት የአካልና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ጋር ተዛምዶ በአንዳንድ እናቶች ላይ የሚያጋጥም ነው ፡፡

የድባቴ መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

የድባቴ ሕመም መንስኤ ይሄ ነው ብሎ በእርግጠኝነት ለመናገር ያዳግታል፡፡ ኾኖም የመስኩ ተመራማሪዎች ለድባቴ ሕመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን እንደሚከተለው ይዘረዝሯቸዋል፡፡

• በዘር የመጣ ከኾነ

• አዕምሮን የሚረብሽ ከባድ የሕይወት አጋጣሚ

• የሚወዱት ሰው በሞት መለየት

• ከሰዎች ጋር ያለ ሠላማዊ ግንኙነት መናጋት

• አዕምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የኾነ ሀሳብና ሁኔታ ሲገጥም በተጨማሪም ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት በሚከሰት የአዕምሮ ጉዳት፣ ጭንቀት፣ መገለልና የሞራል ውድቀት ምክንያት ለድባቴ ከሌላው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡

ድባቴን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

የሚከተሉትን ጤናማ የአኗኗር መንገዶች በመከተል ድባቴን ሳይባባስ ማቆም ይቻላል፡፡

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤

• ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መመስረት፤

• ከአልኮል፣ ከትምባሆ እና ከአደንዛዥ እፆች መቆጠብ፤

• አሉታዊ ሀሳቦችን ከአዕምሮ አስወግዶ አዎንታዊ ጎኖችን ማሰብ መለማመድ፤

• በህይወት ውስጥ ለችግሮች ፍፁም የሆነ መፍትሄ እንደሌለ ማስታወስ፤

• የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለማለፍ በትዕግስት ጠንክሮ መስራት፤

• ለሳቅ ለጨዋታ በአጠቃላይ ለመዝናኛ ጊዜ ማበጀት፤

• ለሰዎች በጎ ነገር በማድረግ መልካም ወዳጅነት ማፍራት፤

• ጭንቀትና ስጋትን ለቅርብ ሰው ማካፈል፤

አንድ ሰው የድባቴ ስሜት ሲሰማው ከላይ የተዘረዘሩትን ሞክሮ መሻሻል ካላሳየ ሕክምና በወቅቱ መጀመር ይገባዋል፡፡ የድባቴ ሕመም ያጋጠመው ሰው መድሃኒቱን በአግባቡ ከተከታተለና ተገቢውን ሕክምና ከባለሞያዎች ካገኘ ምርታማ እና ለሚኖርበት ማኅበረሰብ ትርጎም ያለው አስተዋፅዖ ማድረግ ይችላል፡፡ ሕክምና ካላገኘ ግን ምልክቶቹም እየጨመሩና ሕመሙም እየተባባሰ ይመጣል፡፡ ሕክምናው ውጤታማ እንዲኾን ደግሞ ሰዎች ሃሳቦቻቸውንና ጭንቀቶቻቸውን ከሐኪሞቻቸው ጋር በግልፅ መነጋገር ግድ ይላቸዋል፡፡

ሕክምና የሚያስፈልገው መቼ ነው? አንድ ሰው የድባቴ ስሜት በዕለት ተዕለት ጤናማ አኗኗሩ ላይ እክል የሚፈጥር ከኾነ የሕክምና እገዛ ያስፈልገዋል፡፡ በተለይም ታማሚው ራሱንም ኾነ ሌሎችን የመጉዳት አዝማሚያ ካሳየ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ማንኛውም የጤና ተቋም ዘንድ ሄዶ የመድሃኒት ወይም የሌላ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ሊረዳ ይገባል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...

“ሎዛ ዘፀአት”እና “የሎዛ ድርሳናት”ተከታታይ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍት ተመረቁ

በጋዜጠኛና ደራሲ መርዕድ እስጢፋኖስ የተጻፉት ሎዛ ዘፀአት(2014 ዓ.ም) እና...