የሐገር ባለውለታው ደራሲ ሀብታሙ የተከበረበት ልዩ ቀን

Date:

ደራሲና መምህር ሀብታሙ አለባቸው “ቤት እንደሚያስፈልገው ብቻ ሳይሆን እንደሚገባው በማመን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሀገር ባለውለታው ደራሲና መምህር ሀብታሙ አለባቸው ያለቀና ፈርኒሽድ የተደረገ ባለ ሁለት መኝታ ቤት በስጦታ አበርክተውለታል::

ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ዛሬ ከሐገር ባለውለታዎቹ አንዱ ሆኖ በክብር ከአዲስ አበባ መስተዳድር ከንቲባ አዳነች አበቤ እንዲሰጠው ለማድረግ ብዙ የደከሙ አሉ:: ከእነዚህ ሰዎች መካከል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ የሆኑት ተ/ፕ ነብዩ ባዬ አንዱ ነው::


ሐብትሽ ቤት ማግኝት ከምንም ዋናው ጉዳይ መሆን እንዳለበት ከነባ ጋር ከተወያየን በኃላ እረፍት ሳልነሳው አልቀርም:: የሐብትሽ የቤት ጉዳይ በተመለከተ እኔ ጋር ወንድሙ ሙሉቀን እንዴት ሆነ እያለ ይደውላል:: ግዴለህም አንዴ መስመር ይዟል:: እያልኩት ቆየሁ:: እኔም ደግሞነባን ስልክ በመደወል በቴክስትም በአካልም ሳገኝው ጉዳዩ ከምንደረሰ እያልኩ መጎትጎቴ አልቀረም::

የሆነው ሆኖ ትላንትና አመሻሽ ላይ ነባ እጅግ ደስ የሚል ዜና አበሰረኝ:: ከንቲባ አዳነች አበቤ ለእርሱ የሚሆነውን ቤት እራሳቸው ሄደው በማየት ለታላቁ የሐገር ባለውለታው ደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ቤት እንዲሰጠው አድርገዋል:: እንኳን ደስ ያለህ! አለኝ:: እጅግ ደስታ በተሞላበት አንደበት::እኔም እሱን ከልቤ አመሰገንኩት:: እሱ ደግሞ እኔን ያመሰግናል:: ለማንኛውም የዛሬው ቀን ለእኔ ልዩ ቀን ነው::

በድጋሚ ይህን ታላቅ ተግባር እውን ላደረጋችሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ : የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ የሆኑት ተ/ፕ ነብዩ ባዬ እንዲሁም ለላፍቶ ክ/ከተማ አስተዳደር እና ዋናሥራ አስፈፃሚን በደራሲ ሐብታሙ አለባቸው ስም ከልብ እናመሰግናለሁ::

በመጨረሻም የዛሬው የሐብታሙ ቤት እውን እንዲሆን በጋራ ለደከማችሁ የጊዜ ሆስፒታል ዳይሬክተሩ ፍሬው :ሙሉቀን እና መሰረትን አመሰግናለሁ:: ሐብትሽ ከዚህ በኃላ በቅርቡ በአዲስ ስራ እንገናኛለን ብሎናል!!! እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ::

(ይትባረክ ዋለልኝ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...