የመንግሥት ዕዳ አንድ ትሪሊዮን ብር አለፈ

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት፣ በአጠቃላይ ካለው የብድር ክምችት አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ የመንግሥት መሆኑን አስታወቀ።

መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ለቋሚ ኮሚቴውና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የባንኩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የባንኩ የብድር ክምችት 1.393 ትሪሊዮን ብር መድረሱንና ከዚህ መጠን ውስጥ 74.4 በመቶ ወይም አንድ ትሪሊዮን ብር የመንግሥት ዕዳ መሆኑን ገልጸዋል።

ለፓርላማ የቀረበው የስምንት ወር አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚጠቁመው፣ የባንኩ ጠቅላላ የብድርና ቦንድ ክምችት (outstanding loans and bonds) መጠን ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ የተሻገረ ሲሆን፣ ከዚህም ላይ የግል ተበዳሪዎች ድርሻ ከ3ዐዐ ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተጠቅሷል።

ከተገለጸው አጠቃላይ የብድር ክምችት መጠን በቦንድ የተወሰደ ብድር 66.7 በመቶ ያህሉን በመሸፈን የአብላጫውን ድርሻ ሲወስድ፣ 27.62 ቢሊዮን ብር የተጠራቀመ ወለድ መሆኑም ተገልጿል።

ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ ያሳየውን የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ አቤ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 15 ዓመታት የገበያ መር የፋይናንስ አቅርቦት (commercial finance) እየተወ፣ ለመንግሥት ትልልቅ ፕሮጀክቶች በትንሽ ወለድ ብድር ሲያቀርብ ነው የቆየው። እኔ ፕሬዚዳንት ሆኜ የዛሬ ስምንት ዓመት ባንኩን ስቀላቀል ከነበረው አጠቃላይ ብድር ለግል ዘርፉ የተሰጠው ብድር ስምንት በመቶ ብቻ ነበር። የተቀረው 92 በመቶ በመንግሥት የተወሰደ ነው። መንግሥት ከወሰደው ብድር 98 በመቶ የሚሆነው የተሰጠው በስምንት በመቶ የወለድ ምጣኔ ሲሆን፣ የተቀረው ሁለት በመቶ ብቻ በ11 እና በ12 በመቶ የወለድ ምጣኔ የተሰጠ ብድርነው፤›› ብለዋል።

መንግሥት በወሰደው ብድር ላይ 173 ቢሊዮን ብር ወለድ መጠራቀሙንና መንግሥት ግን ብድሩን ባያቃልልም፣ ንግድ ባንክ ወለዱን መሰብሰቡ ታሳቢ ተደርጎ በየዓመቱ ግብር ሲከፍል መቆየቱን ገልጸዋል።
ከሪፖርተር ጋዜጤ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ሥልጠና አከናወነ

ኩባንያችን ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመተባበር...

የኔታንያሁ ድንገተኛ ማስጠንቀቂያ እና የቢሊዮን ዶላር የጋዝ ሚስጥር!

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከታሪካዊቷ የግብፅ ምድር የሚሰማው...

ኤርትራ ሠራዊቷን በአስቸኳይ ከግዛቷ እንድታስወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንድትሆን ኢትዮጵያ ጠየቀች

የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጣሯቸዋል ካላቸው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች እንዲወጣ እና...

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞች ቁጥሩ ከ5.46 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2018 አ.ም የስድስት ወር የዕቅድ አፈፃፀሙን...