የረመዳን ወርን ከድሆች፣ ችግረኞች እና ስደተኞች ጋር በጋራ በመብላት፣ በመጠጣትና በመደገፍ ማሳለፍ ይገባል ሲሉሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ አስገነዘቡ።
6ኛው ሀገራዊ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
ሼኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አንድነትን በተግባር የሚያሳየው የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ ግብር አስደሳች መሆኑን ገልጸው÷ የረመዳን ወር የቸርነት ወር በመሆኑ ከድሆች፣ ችግረኞችና ስደተኞች ጋር በጋራ ማሳለፍ ይገባል ብለዋል።
የእምነቱ ተከታዮች ለሀገራችን፣ ለወገናችን፣ ለአፍሪካ እና ለዓለም ሰላም ዱዓ ማድረግ ይገባል ብዋል።
በመርሐ ግብሩ ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የሐይማኖቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
