ማህበሩ የገዠውን መብት ለማስጠበቅ ከአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት ለመተግበር የመግባብያ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓት አድርጓል ።
የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የሚሰራው የገዢውን መብት መጠበቅ ስለሆነ ዘርፉን በህግ ቢቻ እንዲመራ ሰፊ ስራዎች እየሰራሁ እገኛለሁ ብሏል።
የገዢውን መብት ሲጠበቅ የሻጭም መብት መጠበቅ ነው ብለን እናምናለን ብሏል።
ገዢው በዚህ ሴክተር ያለው እምነት ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ በመምጣቱ ቀጣይ የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት በግልግል ዳኝነት ለፍትህ ሚኒስቴር የጠየቅን ቢሆንም አዋጁ የፀደቀ ቢሆንም የአፈፃፀም መመሪያ ስላልተዘጋ ለጊዜው ማግኘት አልቻልንም፡፡
የአዲስ አበባ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ ገዝዎች ከገጠማቸው ችግር አኳያ ግዜ የማይሰጠው መሆኑ ገልጸዋል።
አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ላለፉት በርካታ አመታት የሰራበት ሁኔታ ስላለ ጥያቄው በታላቅ ደስታ ተቀብለናቸዋል ብለዋል።
ስምምነቱ ያስፈለገው ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ በገዢና በሻጭ በኩል ያሉ አለመግባባች ተጨማሪ ፍ/ቤት ሄደው ሳይንገላቱ እንዲፈቱ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።
የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ከተማ እንደተናገሩት ማህበራችን በዋነኝነት የሚሰራው የገዢውን መብት መጠበቅ ስለሆነ ዘርፉን በህግ ቢቻ እንዲመራ ሰፊ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የገዢውን መብት ሲጠበቅ የሻጭም መብት መጠበቅ ነው ብለን እናምናለን ብለዋል።
ከዚህ አዲስ አዋጅ 1357/2017 በፊት ሴክተሩ የህግ ማዕቀፍ ያልነበረው በመሆኑ ሪል እስቴት ሴክተር ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲገባ አድርጎት መቆየቱን ተናግረዋል።
ገዢው በዚህ ሴክተር ያለው እምነት ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ በመምጣቱ ቀጣይ የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት በግልግል ዳኝነት ለፍትህ ሚኒስቴር የጠየቅን ቢሆንም አዋጁ የፀደቀ ቢሆንም የአፈፃፀም መመሪያ ስላልተዘጋ ለጊዜው ማግኘት አልቻልንም ነው ያሉት፡፡
ነገር ግን ገዢዎች ከገጠማቸው ችግር አኳያ ግዜ የማይሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ላለፉት በርካታ አመታት የሰሩበት ሁኔታ በመኖሩ ጥያቄ አቅርበን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል።
ስምምነቱ ለምን አስፈለገ?
👉ስምምነቱ ያስፈለገው ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ በገዢና በሻጭ በኩል ያሉ አለመግባባች ተጨማሪ ፍ/ቤት ሄደው ሳይንገላቱ እንዲፈቱ ለማስቻል መሆኑን ተገልጿል።
👉የገገዢውን መብት ለማስጠበቅ እና የሪል እስቴት ሴክተሩን ገጽታ ለመገንባት ጥቂት ስነ-ምግባር የጎደላቸው አልሚዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ።
👉በኢትዮጵያ ጤናማ የሆነ የሪል ስቴት ሴክተር እንዲኖር
👉በገዢና እና በሻጭ በኩል ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚከተላቸው ስትራቴጂ የጸደቀውን አዋጅ 1357/2024 ወደ ተግባር ለማስገባት ነው
👉ቀጣይ ከወራት በኋላ የሚጸድቀውን ደንብ ለማስተግበር ያለውን ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ከተመሰረተ ዘጠኝ ወር ያስቆጠረ ሲሆን እየሰራቸው ያሉ ተግባራት በርካታ ናቸው።
