የሊቢያው የቀድሞ መሪ ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ በጥይት ተመትቷል። በአንድ ወቅት የአባታቸው አልጋ ወራሽ ሆነው ይታዩ የነበሩት የ53 አመቱ ግለሰብ መሞታቸውን ከፖለቲካ ቡድን መሪዎች ማረጋገጡን የሊቢያ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ጠበቃቸው ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት “አራት ሰዎች ያለው የኮማንዶ ቡድን” በዚንታይን ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ግድያ ፈጽመዋል፣ ከጥቃቱ ጀርባ ማን ሊኖር እንደሚችል ግን አልታወቀም።
የሟቹ እህት ለሊቢያ ቲቪ እንደተናገረችው ከአልጄሪያ ድንበር አቅራቢያ መሞቱን አስታውቃለች።እ.ኤ.አ. ከ1969 ጀምሮ ሊቢያን ሲመሩ የቆዩት አባታቸው በ2011 በተነሳው ህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ተወግደው እስከ ከተገደሉቡት ጊዜ ድረስ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው እና የሚፈሩ ሰው ሆነው ይታዩ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1972 የተወለዱት ሰይፍ አል እስላም እ.ኤ.አ. ከ2000 ጀምሮ የጋዳፊ አገዛዝ እስኪወድቅ ድረስ ሊቢያን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለነበራት መቀራረብ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።
አባታቸው ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ – በፀረ-መንግስት ተቃዋሚዎች ጭካኔ የተሞላበት ጭቆና ውስጥ ቁልፍ ሚና ነበራቸው በሚል ተከሰዋል። በዚንታን ከተማ በተቀናቃኝ ሚሊሻ ለስድስት ዓመታት ያህል በእስር መቆየታቸው ይታወሳል።
#ዳጉ_ጆርናል
