የቃል ኪዳን ታቦቱን የሚያቃልል ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ያሰራጩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

Date:

በ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር ወቅት በጋሞና አካባቢው  ዞኖች ሀገረ ስብከት በቁጫ ወረዳ ያጋራ ቀበሌ የቃል ኪዳኑን ታቦት እና የእምነቱን ሥርዓት በሚያቃልል መልኩ በቲክቶክ (TikTok) ምስልና ቪዲዮ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው።

ሕዝቅኤል ማጃ እና መርዶክዮስ ማጃ የተባሉ ግለሰቦች የሃይማኖትን ሰላምና ስሜት በመንካት (በ1997 የወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 492(ለ) መሠረት) የቁጫ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ተከሳሾቹ ጥፋታቸውን መከላከል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ በ 1 ዓመት ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

የጋሞና አካባቢው  ዞኖች ሀገረ ስብከት እንደገለጸው ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ሰባኪ እና ይቅር ባይ ብትሆንም፣ እንዲህ አይነት ፀያፍ ድርጊቶች በሕግ አግባብ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጽዋል። ይህ ውሳኔ ለሌሎች መሰል ድርጊት ለሚፈጽሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ትምህርት እንደሚሆን አስታውቋል ።

©  የጋሞና አካባቢው  ዞኖች ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምግባረ-መልካሙ ኢትዮጵያዊ

ስለሺ መንገሻ - ከ1934 እስከ 2018 ዓ.ም ሠሎሞን ለማ ገመቹ. ግዮን...

ትራምፕ ለኔታንያሁ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ...

ኤምባሲዎችና የውጭ ባለሀብቶች በ«ፍራንኮ-ቫሉታ» ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ...

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ከዓመታዊ የትርፍ 90 በመቶውን እንዲያከፋፍሉ ሊደረግ ነው

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ተብለው የሚቋቋሙ ፈንዶች ከዓመት ትርፋቸው ቢያንስ...