በጉብኝታቸውም የሃይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩን አግኝተው ተወያይተዋል፡፡
መላው የራይድ አስተዳደር አባላትም ክቡር አምባሳደሩን በክብር ተቀበለው ተዋውቀዋቸዋል፡፡
በወቅቱ ከአባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም አምባሳደሩ ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡
የተከበሩ አምባሳደር፣ ድርጅታችንን ስለጎበኙና የድርጅታችንን አባላት በመልካም መንፈስ ስላነቃቁልን በመላው የራይድ ቤተሰብ አባላት ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
