የቲክቶክ መተግበሪያን ከስልካቸው የሚያጠፉ አሜሪካዊያን ቁጥር ጨምሯል

Date:

ቲክቶክ የአሜሪካ የጣምራ ድርጅቱን ይፋ ካደረገ በኋላ በአማካይ በየቀኑ መተግበሪያውን የሚያጠፉ የአሜሪካ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከባለፉት ሶስት ወራት አንፃር በ150% መጨመሩ ተዘግቧል።

በርካታ የአሜሪካ ተጠቃሚዎች የቲክቶክ አዲሱ ፖሊሲ የሰዎች የዘር ማንነትና ምንጭን መረጃ እንደሚሰበስብ የገለጹ ሲሆን፣ በተጨማሪ ስደተኛና ዜጋ መሆናቸውን እንደዚሁም ወሲባዊ ህይወትን በተመለከተ መረጃ ይሰበስባል ብለዋል።

ይህም በርካታ ተጠቃሚዎች የአሜሪካው የቲክቶክ ተቋም ይፋ ከሆነ በኋላ መተግበሪያውን እንዲያጠፉ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

ሌሎች ተጠቃሚዎች ደግሞ ቪዲዮ በሚለቁበት ወቅት ችግር እንደገጠማቸው ሲገልጹ የአሜሪካው ተቋም ችግሩ በአሜሪካ የዳታ ማዕከል ላይ ባጋጠመ ችግር መከሰቱን ገልጿል።

የቲክቶክ መተግበሪያ መጥፋትን ተከትሎ የተፎካካሪዎቹ የአፕስክሮልድ መተግበሪያን የሚጭኑ ሰዎች በአስር እጥፍ ሲጨምር፣ የስካይላይት ሶሻል በ919% እንደዚሁም የሬድኖት ደግሞ በ53% በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጨምሯል።

ዘገባው የሲኤንቢሲ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...