የቲክቶኮ ድምቀት በመድረክ ትያትር መጣ!

Date:



ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው በኢትዮጵያ የድራማ ታሪክ ውስጥ በአዲስ አይነት መንገድ የመጣ ምርጥ ተዋናይ ደራሲና አዘጋጅም ጭምር ነው።

( በአሌክስ ዘመላክ)

ፍላሎት ፣ ትራፊኳና ከአፍ ሰመያመልጥ የተሰኙ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፏል እንዲሁም አዲስ ድባብ ፤ደባል አማች፤የእቴጌ ማጀት ፤ጎረቤታሞቹ የተሰኙ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች የተወሰኑት ላይ በፅሁፍ በዝግጅት የተሳተፈ ሲሆን ሁሉም ላይ የትወና አቅሙን አሳይቷል ።


ቴዎድሮስ ከቅርብ ጊዜአት ወዲህ ዘመኑ በፈጠረለት የ ቲክቶክ ፕላትፎርም በመጠቀም እጅግ በተዋበ መንገድ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዩችን በማንሳት በድራማ መልክ በማቅረብ ተወዳጅነትን እያተረፈ ይገኛል።

ባሳለፍነው ሰኞ ሃምሌ 13/2018 ዓም በአለም ሲኒማ የተመረቀው መልቲ ትያትር ላይ ከሌሎች ምርጥ ተዋናዮች ጋር በመሆን ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል ።የሰውነቱ ቀጠን ማለት መድረክ ላይ እንዳይታይ አላገደውም ይልቁንም መድረኩ ላይ ገዝፎ ይታያል ።
የኮሜዲ ዘውግ ያለው “መልቲ” ትያትር በመልቲ የትያትር ቡድን ተደርሶ በስንታየሁ ታዬ (ፋቡላ) የተዘጋጀ ነው።


የታሪክ ማጠንጠኛውን በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ያደረገው ትያትሩ ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ ቴአርትና ባህል አዳራሽ-ማዘጋጃ ቤት ለዕይታ በቅቶ በተመልካቾች ዘንድ ከፍ ያለ አድናቆትና ተወዳጅነትን ማግኘት ችሎም ነበር።

ዘመኑን በሚመጥንና በአዳዲስ ሀሳቦች ዳግም የተዘጋጀው ትያትሩ ምትኩ በቀለ፣ ኤልሻዳይ ከበደ፣ ሱራፌል ብስራት፣ ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው፣ አቤል ሰለሞን ፣ እየሩሳሌም ነስሩና ፌቨን ኪዳነ ማሪያም ይተውኑበታል።

መልቲ ዘወትር ሰኞ በ 12:00 ሰዓት በዓለም ሲኒማ ለዕይታ ይበቃል።

ከይትባረክ ገፅ የተወሰደ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...