የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ይፋ አደረገ

Date:

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከአሁን በፊት ከሦስተኛ ክፍል ይጀምር የነበረው ወደ ሰባተኛ ክፍል እንዲዘገይ ተደርጓል።

በተጨማሪም በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት ያልነበረው የግብረ-ገብ ትምህርት በአዲሱ ካሪኩለም መካተቱን ቢሮው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የትግራይ ትምህርት ቢሮ መረጃ፣ ” በክልሉ ሲተገበር የቆየው ስርዓተ ትምህርት 16 ዓመታትን ያስቆጠረ ” መሆኑን ገልፆ ፤ ” ስርዓት ትምህርቱ የክልሉን ራዕይ ለማሳካት ከሚደረገው ጥረት ጋር በበቂ ሁኔታ የተጣጣመ አስተዋፅኦ አላበረከተም ” ብሏል።

ቢሮው እንዳስታወቀው፣ የትምህርት ስርዓቱን ከዘመኑ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ በመሆኑ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተለወጠውን ዘመናዊ ዓለም የሚመጥን ስርዓተ ትምህርት መቅረፅ ወሳኝ ነው።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ14 የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ባለሙያዎች መዘጋጀቱን ቢሮው ገልጿል።

በስርዓተ ትምህርቱም ከአካባቢው ተሞክሮ በተጨማሪ ከእስያ የስነ-ምግባር ትምህርት፣ ከስካንዲኔቪያና ከሰሜንና ምዕራብ አውሮፓ ደግሞ እኩልነትና ተጠያቂነትን የሚመለከቱ ተሞክሮዎች መካተታቸውን አስታውቋል።

ቢሮው ” አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ለመቅረፅ ዩኒሴፍ 550 ሺህ ዶላር ፈቃድ ቢሰጥም፣ የፌዴራል መንግሥት በጀቱን ሙሉ በሙሉ ባለመልቀቁ እስካሁን ለስራው የዋለው 200 ሺህ ዶላር ብቻ ነው ” ብሏል።

የ2019 ዓ.ም. የመማርና የማስተማር ሂደት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንደሚከናወን የትምህርት ቢሮው አስታውቋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...