በቻይና ወታደራዊ አመራር ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ድንጋጤ ተፈጥሯል።
የፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የቅርብ ወዳጅ እና የሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን የሆኑት ጄነራል ዣንግ ዩዢያ. በከፍተኛ የሀገር ክህደት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተሰምቷል።
የኑክሌር ምስጢር ሽያጭ፦ ጄነራሉ የቻይናን እጅግ ሚስጥራዊ የሆኑ የኑክሌር ቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለአሜሪካ አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ከፍተኛ ሙስና፦ በጦር ኃይሉ ውስጥ ለሹመትና ለደረጃ ዕድገት ከፍተኛ ገንዘብ ሲቀበሉ እንደነበር ተደርሶበታል ተብሏል።
የአመራር ክፍተት፦ ከጄነራሉ ጋር በመሆን ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ይህ እርምጃ ቻይና ከአዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር ለምታደርገው የንግድና የደህንነት ንግግር በምትዘጋጅበት ወሳኝ ወቅት የተከሰተ በመሆኑ ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል።
