Home Featured የቻይና አምባሳደር ከኦሞቲክ መስራች አቶ ኢያሱ ጋር ተወያዮ

የቻይና አምባሳደር ከኦሞቲክ መስራች አቶ ኢያሱ ጋር ተወያዮ

የቻይና አምባሳደር ከኦሞቲክ መስራች አቶ ኢያሱ ጋር ተወያዮ

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሀይ የተመራ የኢንቨስተሮች ልዑክ ከኦሞቲክ ግሩፕ መስራችና ባለቤት እንዲሁም ከአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ፕረዝዳንት ከሆኑት አቶ ኢያሱ ወሰን ጋር ተወያዩ።

‎በቻይና አምባሳደር ቺን ሀይ የተመራው ልዑክ አርባምንጭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልል እና የዞን የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ላይ ተወያይተው ተፈራርመዋል።


ከልዑኩ ጋር በሆቴል፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ በግብርና እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት የሁለትዮሽ ትብብር ላይ የተወያዩት አቶ ኢያሱ ወሰን ፤ ኢንቨስተሮቹ ጋር በጋራ ለማልማት ከስምምነት ደርሰዋል።

በጋሞ ዞን እና በጠቅላላው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ እምቅ ሃብቶችን እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለልዑኩ ያስረዱት አቶ ኢያሱ “በርካታ ኢንቨስትመንቶች ላይ በመሰማራት አከባቢውን ማልማት እና ግዙፍ የስራ ዕድል መፍጠር እንችላለን” ሲሉም ገልፀዋል።


‎አምባሳደር ቺን ሀይ እና የቻይና ባለሀብቶቹም ከአቶ ኢያሱ ወሰን እና መሰል ባለሀብቶች ጋር መስራት የሚችሉበት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በመመያየት ፍላጎታቸውን ገልፅው በቀጣይ ጥናቶችን በማድረግ ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከስምምነት ተደርሷል።