የአሜሪካን 250ኛ ዓመት የነጻነት በዓል አከባበርን “ከልውውጥ ኘሮግራም” ተሳታፊዎች ጋር በይፋ አስጀመረ

Date:

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የአሜሪካን 250ኛ ዓመት የነጻነት በዓል (#Freedom250) ምክንያት በማድረግ የተዘጋጁ የዓመቱን ዝግጅቶች፣ በኤምባሲው የልውውጥ ፕሮግራሞች ላይ ከተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን በዚህ ሳምንት በይፋ አስጀምረዋል።

አምባሳደሩ በ2024 እና 2025 የልውውጥ ፕሮግራሞች ተሳታፊ ለነበሩ ወጣቶች እና ባለሙያዎች በመኖሪያ ቤታቸው የአቀባበል እና የእራት ግብዣ ያደረጉ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ የቀድሞ ተሳታፊዎች እርስ በርስ የሚገናኙበትና ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት የሚያድሱበት መድረክ ሆኖ አልፏል።

አምባሳደር ማሲንጋ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ የልውውጥ ፕሮግራሞች የአሜሪካን የቴክኖሎጂ፣ የስራ ፈጠራ እና የትምህርት ጥራት ለማሳየት ያላቸውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ብቃት ያላቸውን መሪዎች በመደገፍ ሽርክናችንን እናጠናክራለን፤ ተጨባጭና የሚለካ ውጤትም እናመጣለን” ያሉት አምባሳደሩ፣ “ጠንካራ ተቋማት፣ በችግር የማይበገሩ ማህበረሰቦች እና እያደገ ኢኮኖሚ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአሜሪካ ጠቃሚ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የአልሙናይ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሶፎኒያስ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በዓሉ ትርጉም ያለው መልእክት እንዳለው ገልጸዋል።

“ይህ አሜሪካ የ250ኛ ዓመት የነጻነት በዓል (#Freedom250) የታሪክ አከባበር ብቻ አይደለም። ለልውውጥ ፕሮግራም ተሳታፊዎች፣ ያገኙትን ልምድ ወደ ተግባር በመቀየር ማህበረሰቡን እንዲጠቅሙበት የተሰጠ ኃላፊነት ጭምር ነው” ብለዋል።

ኤምባሲው ይህንን ታሪካዊ በዓል አስመልክቶ በ2026 ዓ.ም በሙሉ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን እንደሚያሰናዳ የገለጸ ሲሆን፣ ስለ ዝግጅቶቹ እና ስለ አልሙናይ ፕሮግራሞች ተጨማሪ መረጃዎችን በድረ-ገጻቸው ላይ ማግኘት እንደሚቻል ጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...