የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ታደሙ

Date:

የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው በቢሾፍቱ በተካሄደው የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማጠቃለያ መርሐ-ግብር ላይ ታድመዋል።

ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው በተጨማሪ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኸርቪን ማሲንጋ ተገኝተዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ለእንግዶቹ በአየር ኃይል ግቢ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንግዶቹ የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የአቪዬሽን ኤክስፖ የጎበኙ ሲሆን የክብረ በዓሉ የማጠናቀቂያ ዝግጅት ላይ ታድመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...