የአእላፋት ዝማሬ በኡጋንዳ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በልዩ ድምቀት ተካሂደ

Date:

የ2018 ዓ.ም የአእላፋት ዝማሬን እንዲያዘጋጁ በዋና አዘጋጆች ፈቃድ ከተሰጣቸው በውጭ ሀገር ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የካምፓላ መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ነው።

የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዋና አዘጋጆች ጋር በመነጋገር የካምፓላ መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የ2018 ዓ•ም የአእላፋት ዝማሬን እንዲያቀርቡ እንዲፈቀድ በደብዳቤ በመጠየቅ እና ለዝግጅቱ እውቅና በመስጠት በዋና አስተባባሪነት ዝግጅቱ እጅግ የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

በእለቱ በካምፓላ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ሊቃውንት አባቶች ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች  እጅግ ብዙ ምእመናን የዝማራው ዝግጅት ላይ ተገኝተው በመወለዱ የሰው ልጆችን ሁሉ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ያሸጋገረውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በልዩ ዝማሬ እና እልልታ አክብረዋል።

የካምፓላ መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሚዲያ ክፍል
EOTCTV ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...