የአዉሮጳ ሕብረት ሚንስትሮች በእስራኤል ላይ የጋራ አቋም መያዝ ተስኗቸዋል

Date:


የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ እስራኤል በጋዛ ፍልስጤሞች ላይ በትፈፅመዉ በደል ምክንያት ሕብረቱ በእስራኤል ላይ መዉሰድ ሥላለበት ርምጃ እየተነጋገሩ ነዉ።

ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ከተሰበሰቡት ሚንስትሮች አብዛኞቹ እስራኤል በጋዛ ፍልስጤሞች ላይ በምታደርሰዉ በደል ሕብረቱ ከእስራኤል ጋር ያደረገዉን የሰብአዊ መብት መከበር ስምምነትን ጥሳለች ብለዉ ያምናሉ።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ የሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ካያ ካላስ እስራኤል ሥምምነቱን በመጣስዋ ሕብረቱ ሊወስዳቸዉ የሚገቡ ያሏቸዉን 10 አማራጭ ርምጃዎች ለተሰብሳቢዎቹ አቅርበዋል።

እርምጃዉ ሕብረቱ ከእስራኤል ጋር ያደረገዉን ሥምምነት ሙሉ በሙሉ ለጊዜዉ ማገድ፣ ከእስራል ጋር የሚደረግ የንግድ ልዉዉጥን መቀነስ፣ በእስራኤል ሚንስትሮች ላይ ማዕቀብ መጣል፣ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብና ያለቪዛ ወደ አዉሮጳ መግባትን ማገድ ይጨምራል።

ይሁንና ዲፕሎማቶች እንዳሉት የ27ቱ አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ባንዱም ላይ የጋራ አቋም መያዛቸዉ አጠራጣሪ ነዉ።አሥሩን አማራጭ ርምጃዎቹ ለተሰብሳቢዎች ያቀረቡት ካላስ ራሳቸዉ ሥለሚንስትሮቹ የ«ዉይይት ሒደት» የማዉቀዉ የለም ብለዋል።

ያም ሆኖ የሕብረቱ ዋና ትኩረት ጋዛ ዉስጥ የተከሰተዉ ሰብአዊ ቀዉስ መሆኑን ካላስ አስታዉቀዋል።ካላስ ከእስራኤል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ሳር ጋር ባደረጉት ዉይይት በረሐብ ለሚሰቃዩት ለጋዛ ፍልስጤማዉያን ተጨማሪ እሕል እንዲገባ መግባባታቸዉን ባለፈዉ ሐሙስ አስታዉቀዉ ነበር።ስምምነቱን ግን እስራኤል እስከ ዛሬ ገቢር አላደረገችዉም።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...