ከ1ኛ እስከ 8ኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁት በቀጥታ ጥሎ ማለፉን የሚቀላቀሉ ሲሆን ከ9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃን የሚያገኙት ደግሞ እርስ በእርስ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 16ቱን ለመቀላቀል ይጫወታሉ።
አርሰናል እና ባየርንሙኒክ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን ቀድመው የተቀላቀሉ ክለቦች ናቸው ፤ ሌሎች 30 ቡድኖች ግን በቀጥታ ማለፋቸውን እና ለጥሎ ማለፍ መብቃታቸውን ለማረጋገጥ የመጨረሻ ፍልሚያቸውን ዛሬ ያደርጋሉ፡፡
ሁሉም የሻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በተመሳሳይ 5 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል። አርሰናል ዛሬ ካይራትን ማሸነፍ ከቻለ በአዲሱ የጨዋታ ቅርጽ ሁሉንም ጨዋታዎች ያሸነፈ የመጀመሪያው ክለብ ይሆናል፡፡
ፒኤስጂ ከኒውካስትል ዩናይትድ፣ሪያል ማድሪድ ከቤኔፊካ፣ ናፖሊ ከቼልሲ፣ ሊቨርፑል ከካራባግ፣ ባየርንሙኒክ ከፒኤስቪ፣ ማንችስተር ሲቲ ከጋላታሳራይ፣ ኢንተር ሚላን ከቦርሲያ ዶርትሙንድ፣ ጁቬንቱስ ከሞናኮ፣ ባርሴሎና ከኮፐንሀገን እንዲሁም አይንትራ ፍራንክፈርት ከቶተንሀም ሆትስፐር ምሽት ከሚደረጉት ተጠባቂ ጨዋታች መካከል ናቸው፡፡
ሻምፒየንስ ሊጉ ደረጃ
1 አርሰናል :- 21 ነጥብ
2 ባየር ሙኒክ :- 18 ነጥብ
3 ሪያል ማድሪድ :- 15 ነጥብ
4 ሊቨርፑል :- 15 ነጥብ
5 ቶተንሀም :- 14 ነጥብ
6 ፒኤስጂ :- 13 ነጥብ
7 ኒውካስትል ዩናይትድ :- 13 ነጥብ
8 ቼልሲ :- 13 ነጥብ
