የአየር ሁኔታ መበላሸት በዋሽንግተን ዲሲ እና በኒውዮርክ የበረራ ስረዛ አስከተለ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዋሽንግተን ዲሲ እና በኒውዮርክ ባጋጠመው አስከፊ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ ስፍራዎቹ የሚደረጉ መደበኛ በረራዎችን መሰረዙን ለክቡራን ደንበኞቹ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ መሠረት በጥር 16 ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው በረራ ቁጥር ET 500 እንዲሁም በጥር 17 ቀን ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሰው በረራ ቁጥር ET 501 ተሰርዘዋል።

በተመሳሳይ በጥር 17 ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ኒውዮርክ የሚደረገው በረራ ቁጥር ET 514 እና ከኒውዮርክ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሰው በረራ ቁጥር ET 515 በአየር ሁኔታው ምክንያት የማይከናወኑ መሆኑ ተገልጿል።

በእነዚህ የበረራ ስረዛዎች ምክንያት ለተቸገሩ መንገደኞች እንደ አስፈላጊነቱ የቦታ ዳግም ምዝገባ፣ የበረራ ጊዜ ሽግሽግ ወይም የክፍያ ተመላሽ አገልግሎቶች እንደሚመቻቹ አየር መንገዱ አረጋግጧል። ተቋሙ ለተጓዦች እና ለበረራ ሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ፣ ለተፈጠረው እንግልትም ልባዊ ይቅርታውን አቅርቧል።

ተጓዦች ወደ አየር ማረፊያ ከመጓዛቸው በፊት የበረራቸውን ወቅታዊ ሁኔታ በአየር መንገዱ ድረ-ገጽ ወይም የሞባይል መተግበሪያ በኩል እንዲያረጋግጡ የተመከረ ሲሆን፣ በተጨማሪም በስልክ ቁጥር +251 11 617 9900 ወይም በኢሜይል Reservation@ethiopianairlines.com በማግኘት ዝርዝር መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...