የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች

Date:

የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 3 እና 4 ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

በምድብ ሦስት ምሽት 2:30 ናይጄሪያ ከ ታንዛኒያ ይጫወታሉ።

በ2013 በአሰልጣኝ ስቴቨን ኬሺ እየተመራች ሻምፒዮን የሆነችው ናይጄሪያ ከ12 ዓመት በኋላ ዋንጫ ለማንሳት ሞሮኮ ደርሳለች።

ታንዛኒያ በአንጻሩ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ አሸንፋ የማታውቅ ሲሆን፥ ዛሬ ምሽት ይህን ለማሳካት ከንስሮቹ ጋር ትጫወታለች።

ምሽት 5 ሠአት ላይ ደግሞ ዩጋንዳ ከ ቱኒዚያ ይገናኛሉ።

ቀደም ብሎ በሚደረግ ጨዋታ በምድብ አራት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ ቤኒንቀን 9:30 ይጫወታሉ።

ኮንጎ በቅርቡ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ናይጄሪያን በማሸነፍ ወደ መጨረሻው ዙር ያለፈች ሲሆን፥ በሞሮኮው ውድድርም ረጅም ጉዞ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ ምድብ የዋንጫ ግምት የተሰጣት ሴኔጋል ከ ቦትስዋና አመሻሽ 12 ሠአትትጫወታለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...