የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን መንግስትን በሚደግፈው ሰልፍ ላይ በአደባባይ ከህዝባቸው ጋር ታዩ።
በአሰር ሺህዎች የሚቆጠሩ የአያቶላህ አሊ ኻሚኒን ስርዐተ መንግስትና አሁናዊ አስተዳደሩን የሚደግፉ ዜጎች ወደ ጎዳና ወተው ድጋፋቸውን አሳይተዋል።
በኢራን መንግስት ላይ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀልበስ እና ድርጊቱን ለማውገዝ ነው ፔዜሽኪያን ከህዝቡ ጋር በቴህራን ጎዳና ላይ የታዩት።
ማሱድ ፔዜሽኪያን ከዚህ ቀደምም ሰላማዊ ሰልፍ ከህዝባቸው ጋር አድርገው በአሜሪካና እስራኤል ላይ ትችት መሰንዘራቸው አይዘነጋም።
አያቶላህ አሊ ኻሚኒም በተቃዋሚዎች ላይ የተነሳውን ሚዛን አስጠባቂ ሰልፍ ለአሜሪካ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው ብለውታል።
በሌላ በኩል ከኢራን ጋር ቢዝነስ የሚያንቀሳቅሱ አገራት ላይ አሜሪካ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ቢዝነስ የሚሰሩ እና ውል ያላቸው አገራት አሁኑኑ የሚተገበር የ25 በመቶ ቀረጥ ይጣልባቸዋል ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ፅፈዋል።
የትራምፕ ውሳኔ የተሰማው በኢራን ላይ ወታደራዊ አማራጮችን እንወስዳለን ካሉ በኋላ ነው።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
