የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነት ተነሱ

Date:

ከተሾሙ 12ተኛ ወራቸውን የያዙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) ከኋላፊነታቸው ተነሱ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የሚያቋቁመው አዋጅ የባለስጣኑ ዋና ዳይሬክተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾም ይደነግጋል።

በዚሁ መሠረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤ አቶ ሳምሶንን የሚተኩ ዕጩ ተሿሚ ማቅረባቸውን ሪፖርተር አረጋግጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤም፣ “ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ ወርቅነህ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ እንዲሾሙ እጠይቃለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ በሥራ ላይ የሚገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ከኋላፊነት የተነሱበትን ምክንያት አይገልጽም።

ወ/ሮ ሐይማኖት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽፈት ቤት በም/ቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ደግሞ በመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በዳይሬክተርነት ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በከፍተኛ አዘጋጅነት ያገለገሉ ናቸው።

ሪፖርተር-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...