የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

Date:


በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ግንቦት 24 ይካሄዳው ተብሎ በሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ኢዜማ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በሚያካሂድባቸው አካባቢዎች ሁሉ እሳተፋለሁ ያለ ሲሆን ምርጫ የዴሞክራሲ ባህል መገንቢያ መሳሪያ መሆኑን አስታዉቋል።

ፓርቲው ላለፉት አራት ዓመታት በምርጫው ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታዉቆ የትግራይ እና የአማራ ክልልን ጨምሮ የምርጫ ቦርድ ምርጫ ለማካሄድ ባሰበባቸው ስፋራዎች ሁሉ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከስሜት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ታቅበው የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ምርጫውን ለምርጫ ዓላማ ብቻ እንዲጠቀሙ እና መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርጫው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...