የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገበያ ድርሻውን ማሳደጉ ተገለፀ

Date:



የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 (2024/25) በጀት ዓመት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት አመርቂ የሥራ አፈፃፀም ያስመዘገበ ሲሆን፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜም በሁሉም የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎች የገበያ ድርሻውን ማሳደግ ችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት  ከ515 ቢሊየን ብር በላይ  ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡን 1.69 ትሪሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን፣ የገበያ ድርሻው 49.6 በመቶ ሆኗል።

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 2.3 ትሪሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም የገበያውን 50.1 በመቶ የገበያ ድርሻ እንዲይዝ አስችሎታል።

ባለፈው በጀት ዓመት በባንኩ ከተከናወኑ የገንዘብ ዝውውሮች 92 በመቶ የሚጠጋው በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም በገንዘብ ደረጃ ከ13 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ43.1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...